የቤቢ መሐመድና የጥቁር አንበሳ ባለሙያዎች ድንቅ ተጋድሎ!
#Ethiopia | በሕክምናው ዓለም ተስፋ መቁረጥና ተስፋ አለመቁረጥ መካከል ያለው መስመር እጅግ ቀጭን ነው።
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተመዘገበው ውጤት ግን የሰው ልጅ ጥረትና የባለሙያዎች ቅንጅት ምን ያህል ተአምር መስራት እንደሚችል ዳግም አስመስክሯል።
የጉዞው መጀመሪያ፦
የ36 ዓመቷ ወይዘሮ መኪያ ከማል እርግዝናዋ ገና ስድስት ወር ከአምስት ቀን (25 ሳምንት) ላይ እያለ ነበር ምጥ የጀመራት። በሳይንሳዊ አገላለጽ “ውርጃ” ሊባል የሚችልና የመኖር ዕድሉ እጅግ አነስተኛ የነበረው ቤቢ መሐመድ ዋቢ፣ በ900 ግራም ክብደት ወደዚህች ዓለም መጣ።
የባለሙያዎቹ ቆራጥነት፦
የመጀመሪያው ርምጃ
እንደተወለደ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የልብና የመተንፈሻ ማነቃቂያ ተደረገለት።
የ3 ወራት ርብርብ፦
ከታህሳስ 7 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በጽኑ ህሙማን ክፍል (NICU) ውስጥ በባለሙያዎች ክትትል ቆየ።
ውጤቱ፦
የሕጻኑ ክብደት ከ900 ግራም ወደ 1.8 ኪሎ ግራም አደገ። ሙሉ የአካል ምርመራ ተደርጎለት ምንም ዓይነት እንከን ሳይገኝበት በጤና ወደ ቤቱ ተሸኝቷል።
”ልጄን በሕይወት ወደ ቤቴ ይዤው እየገባሁ ነው!” — እናት መኪያ በደስታ እምባ የታጀበ ምስክርነት።
#ያለው ጌታነህ
#getu #BlackLionHospital #NICU #MedicalMiracle #BabyMohammed #EthiopianDoctors #HealthCareEthiopia #Hope #AddisAbaba #ጥቁርአንበሳ #ሕክምና #ተአምር #ቤቢመሐመድ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen



Source: GetuTemesgen









No comments yet.