110,000 ሰው በጉጉት የሚጠብቀው አልበም!የዘመናችን ታላቅ የጥበብ ሰው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ፤ መላው ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ጉ…

- Advertisement -
Sidebar AD
110,000 ሰው በጉጉት የሚጠብቀው አልበም!
የዘመናችን ታላቅ የጥበብ ሰው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ፤ መላው ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ጉጉት እና ናፍቆት ሲጠብቁት የነበረውን “ኢትዮሪካ” የተሰኘ አዲስ አልበሙን አሁን በራሱ ትክክለኛ (Official) የዩቲዩብ ቻናል በኩል በይፋ ለህዝብ ጆሮ አድርሷል።
ሰሞኑን ከአልበሙ ጋር ተያይዞ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መታገዱ በሀገሪቱ የፖለቲካ እና የጥበብ ምህዳር ላይ ከፍተኛ አጀንዳ ፈጥሮ የሰነበተ ቢሆንም፤ ቴዲ ግን ይህንን አጓጊ የጥበብ ስራውን እንደ ቃል ኪዳኑ ለህዝብ አበርክቷል።
​ይህ አልበም በውስጡ ምን አይነት ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መልዕክቶችን ይዞ መጣ? መንግስትንስ ያን ያህል ያስደነገጠው የትኛው ግጥም ወይም ዜማ ነው? የሚለው የብዙዎች የማወቅ ጉጉት አሁን በተግባር ምላሽ እያገኘ ይገኛል።
አዲሱ አልበም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትኩሳት እና በማህበራዊ ህይወታችን ላይ የፈጠረው አዲስ ንዝረት ከወዲሁ በየማህበራዊ ሚዲያው ማስተጋባት ጀምሯል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2