አዲስ የአውሮፕላን መለዋወጫ ፋብሪካ ሊመረቅ ነውጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣…

- Advertisement -
Sidebar AD
አዲስ የአውሮፕላን መለዋወጫ ፋብሪካ ሊመረቅ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓለም አቀፉ የቦይንግ ኩባንያ ጋር በመተባበር የገነባው የኤሮስፔስ መለዋወጫዎች ማምረቻ ፋብሪካ መጠናቀቁንና በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንደሚመረቅ አስታውቀዋል። ይህ ግዙፍ ፋብሪካ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ያላትን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ሲሆን፣ በተለይም በዘርፉ በውጭ ሀገር ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ሲል ለቦይንግ ኩባንያ የተለያዩ የአውሮፕላን መለዋወጫ ግብዓቶችን እያመረተ ማቅረብ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን፣ የአሁኑ ፋብሪካ መጠናቀቅ ደግሞ ሀገሪቱ በኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ያላትን ተወዳዳሪነት የሚያጎለብት ነው። ይህ ስኬት ኢትዮጵያ ከአውሮፕላን ተጠቃሚነት ባለፈ ወደ አምራችነትና ላኪነት የተሸጋገረችበትን አዲስ ምዕራፍ የሚያበስር ታሪካዊ እርምጃ ሆኖ ተመዝግቧል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: