ማርቲን ሉተር እና ሙዚቃ

- Advertisement -
Sidebar AD

ሙዚቃ ሰይጣንንና ክፉ መንፈስን የሚያባርር ኃይል አለው- ማርቲን ሉተር

ከቤተክርስቲያን ቅፅር እስከ ዓለማዊው መድረክ

የፕሮቴስታንት ተሐድሶ መሪው ማርቲን ሉተር ከሃይማኖታዊ ለውጥ አቀንቃኝነቱ ባሻገር ለሙዚቃ የነበረው ፍቅርና አመለካከት እጅግ ጥልቅ ነበር።

ብዙዎች “ሙዚቃና ሃይማኖት” ሲባሉ በመካከላቸው ጥብቅ መስመር ለማስመር ቢሞክሩም ሉተር ግን ሙዚቃን በጠባብ ሃይማኖታዊ እይታ ብቻ አይመለከተውም ነበር።

ሉተር ለሙዚቃ የሰጠው ትልቁ ትርጓሜ “የእግዚአብሔር ስጦታ” (Donum Dei) የሚል ነው። ለእርሱ ሙዚቃ የሰው ልጅ የፈጠረው ጥበብ ሳይሆን ፈጣሪ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ ያስቀመጠው ፀጋ ነው።

“ከቃለ እግዚአብሔር ቀጥሎ ሙዚቃን የመሰለ ታላቅ ነገር የለም” በማለት በሁለተኛ ደረጃ ያስቀምጠዋል።

በዚህ አቋሙ ሙዚቃን ከኃጢአት ፍረጃ ነፃ ያወጣዋል።

ብዙውን ጊዜ ሃይማኖታዊ መሪዎች በቤተክርስቲያን እና በዓለማዊ ሙዚቃ መካከል ግድግዳ ያጥራሉ ሉተር ግን ይህንን ግድግዳ አይስማማም ። በወቅቱ በየመንገዱና በየመጠጥ ቤቱ የሚዘፈኑ የሕዝብ ዜማዎችን (Folk songs) ሳይጠላ ይልቁንም እነዚያን ዜማዎች በመውሰድና መንፈሳዊ ግጥም በመግጠም ወደ ቤተክርስቲያን አምጥቷቸዋል።

ለምንድነው ዲያብሎስ ብቻ ምርጥ ዜማዎችን የሚይዘው?” የሚለው ዝነኛ ጥያቄው ማራኪ ዜማዎች ሁሉ ለፈጣሪ ምስጋና ሊውሉ እንደሚገባ ያለውን እምነት ያሳያል።

ሙዚቃ እንደ ስነ-ልቦናዊ ፈውስ

ሉተር ሙዚቃን እንደ ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ብቻ ሳይሆን እንደ አእምሮ ፈውስ ያየው ነበር። “ሙዚቃ የጭንቀትና የሃዘን ጠላት ናት” ይላል።

አንድ ሰው ዓለማዊም ይሁን መንፈሳዊ ሙዚቃ ሲያዳምጥ አእምሮው ከክፉ ሀሳቦች እንደሚላቀቅና ሰላም እንደሚያገኝ በጽኑ ያምን ነበር ለእርሱ ሙዚቃ ሰይጣንንና ክፉ መንፈስን የሚያባርር ኃይል አለው።

ሉተር ማንኛውንም ሙዚቃ “ኃጢአት” የሚለው ሙዚቃው በቀጥታ ለብልግና ለጥል ወይም ለክፋት ሲውል ብቻ ነው። አለበለዚያ ግን ስለ ፍቅር፣ ስለ ተፈጥሮ ወይም ስለ ሀገር የሚዘመሩ ሙዚቃዎችን እንደ ስጦታ ይቀበላል።

ሙዚቃ በራሱ (እንደ ድምፅና ዜማ) ንፁህ ነው ኃጢአት የሚሆነው የሰው ልጅ ለክፉ አላማ ሲጠቀምበት ብቻ ነው ባይ ነው።

ማርቲን ሉተር ሙዚቃን ከሃይማኖታዊ መጋረጃ አውጥቶ ለሰው ልጅ በሙሉ የተሰጠ ታላቅ በረከት አድርጎታል። ዛሬ የምናየው የዘመናዊ ሙዚቃ እድገትና የምዕመናን የጋራ ዝማሬ ባህል፣ የዚህ ታላቅ ሰው የጥበብ አመለካከት ውጤት ነው።

ሙዚቃ ሰውን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ ብቻ ሳይሆን ሰውን ከራሱ ጋር የሚያስታርቅ መለኮታዊ ቋንቋ መሆኑን ሉተር በተግባር አስተምሮ አልፏል።

#MartinLuther #MusicTheology #ProtestantReformation #HistoryOfMusic #FaithAndArt #Ethiopia #YenetaMedia




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: