በትንባሆ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች  በዋናነት ለካንሰር ህመም አጋላጭ ናቸው  ተባለ በትንባሆ ውስጥ ከ7ሺህ በላይ ኬሚካሎች የሚገ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በትንባሆ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች  በዋናነት ለካንሰር ህመም አጋላጭ ናቸው  ተባለ
በትንባሆ ውስጥ ከ7ሺህ በላይ ኬሚካሎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 70 የሚሆኑት ለካንሰር ህመም ተጋላጭነት በዋናነት ተጠቃሽ  መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ  ከፍተኛ  የጤና አደጋዎች ከሚያስከትሉ  መካከል ዋነኛው ትንባሆ መጠቀም ሲሆን ለልብ ህመም፣ ካንሰር፣ የመተንፈሻ አካላት ችግር እና ለሌሎች ከባድ በሽታዎች ከትንባሆ ጭስ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ከመሆናቸው  በተጨማሪም  የማያጨሱ  ሰዎች  በሌሎች ሰዎች ማጨስ ምክንያት የጤና አደጋ ሊያጋጥማቸውይችላል።    
እንዲሁም  በቤት ውስጥ ሲጋራ ማጨስ ለልጆች እድገት መገታት ዋነኛ መንስኤ ሲሆን በትንባሆ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች  በዋናነት ለካንሰር ህመም አጋላጭ መሆናቸውን ተገልፆል፡፡በመሆኑም የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በህግ የተደነገጉ የትንባሆ ቁጥጥር መመሪያዎችን በመተግበር በህዝብ መገኛ ቦታዎች፣ በመስሪያ ቤቶች፣ በሆቴሎችና በተመሳሳይ አገልግሎት ስፍራዎች ትንባሆ እንዳይጨስ እየተቆጣጠረ መሆኑን አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።dagu
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: