#Ethiopia | በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚንየም ፕሮጀክት 11 እና 17 የሚኖሩ ከ12 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ነዋሪዎቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 17.3 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ቮልቴጅ መስመር፣ የ8.4 ኪ.ሜ የመካከለኛ ቮልቴጅ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ መስመርና የ4.1 ኪ.ሜ የመካከለኛ ቮልቴጅ የአየር ላይ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል፡፡
በተጨማሪም 11 ባለ 630 ኬ.ቪኤ ትራንስፎርመሮች፣ 21 ባለ 800 ኬቪኤ እንዲሁም 21 ባለ 1250 ኬቪኤ ትራንስፎርመሮች በአጠቃላይ 53 ትራንስፎርመሮች እንዲተከሉ ተደርጓል፡፡ በተያያዘ ለነዋሪዎቹ 12 ሺህ 100 ቆጣሪዎች ተገጥመዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ከዚሀ በፊት በየ ብሎኩ በተገጠመ ባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ በጋራ ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን በዚህም በኃይል ማነስና መቆራረጥ ሲቸገሩ ቆይተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በተናጠል ቆጣሪ እንዲገጠምላቸው በመደረጉ ከ12 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በቂ ኃይል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡
ሪጅኑ የመስመር ዝርጋታውን በሚያከናውንበት ወቅት ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ስርቆት ማጋጠሙ የተጠቀሰ ሲሆን በአንፃሩ የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ዝርጋተው በወቅቱ እንዲጠናቀቅ ነዋሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተጠቁሟል፡፡
በቀጣይ በአዲስ አበባ ቤቶች በኩል የሚፈፀሙ ክፍያዎች እንደተጠናቀቁ በኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም በተለያዩ ሳይቶች የሚገኙ ነዋሪዎችን በተናጠል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የማድረግ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
Source: GetuTemesgen









No comments yet.