ቤተር ላይፍ ፎር ኦል ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት አደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

ቤተር ላይፍ ፎር ኦል (Better Life for All) ከየኛ ማይክሮፋይናንስ ጋር በጋራ በመተባበር ወጣቶችንና ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት በዛሬው ዕለት ፈጽመዋል።

ይህ የመግባቢያ ስምምነት በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚው ረገድ በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተገልጿል።

በስምምነቱም ሁለቱም ተቋማት በጋራ በማህበረሰብ ልማት እና በኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያላቸውን ተስፋ እና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን ወጣቶችና ሴቶችን ለተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶች ማለትም (ብድር፣ ቁጠባ፣ ሌሎች የገንዘብ አገልግሎቶችን) ተደራሽነትን ማሳደግ፤ ኮላተራል ባለመጠየቅ ወይም ቀላል መስፈርት ያላቸው ብድሮችን በማቅረብ፤ የሙያ እና የኢንተርፕርነርሺፕ ስልጠናዎች በመስጠት፡ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችን በመደገፍ፣ የፋይናንስ እውቀት በማስጨበጥ፣ የተቋማት አቅም ግንባታ እና አጋርነት በማጠናከር ሁለቱም ተቋማት በጋራ ለመስራት እቅድ እንዳላቸው ገልፀዋል።

አቶ ከተማ ባህሩ የቤተር ላይፍ ፎር አል ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር እንደተናገሩት በአስራ ሶስት ዓመት የስራ ቆይታዉ በርካታ ወጣቶችን በተለያዩ ዘርፎች በማስልጠን ወደ ስራ የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸተቸውን የገለፁ ሲሆን በዚህም በሚቀጥለው አምስት አመት ውስጥ 100 ሺህ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ቤተር ላይፍ ፎር ኦል (Better Life for All) በዚሁ የጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የህግ ባለሞያና ሞዴል እንዲሁም የህክምና ተማሪዋን ሩት ሸዋ ታጠቅን የድርጀቱ ብራንድ አምባሳደር በማድረግ ሾሟል።

በሚያዝያ 9/2018 ዓ.ም






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1