የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ “ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በ

- Advertisement -
Sidebar AD

የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ “ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው፡፡

ለእርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተት የቻለ የበደለውም በደል ሳይኖር፣ ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሠ መድኃኔ ዓለም በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ” በማለት ገለጸው፡፡ በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በስጋው ግን ሞትን ቀመሰ፡፡ የአዳምን ሞት በሞቱ ሊሽር መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን በገዛ ፈቃዱ አሳልፎ ሰጠ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንደሚያድነን በመጀመሪያ ለአዳም ቃል ገባለት፡፡ ከዚያም በነቢያት ትንቢት አስነገረ፡፡ በስጋ በተገለጠ ጊዜም የሰቀሉትና የገደሉት አይሁድ ሳይቀሩ እንዲናገሩ አፋቸውን አስከፈታቸው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን… አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን” ይላል፡፡ “ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፣ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች በአንድነት እንዲሰበስባቸው መጥቷል እንጂ።” ተብሎ ተጽፏልና፡፡ በድንቅ ተዋህዶ አምላክ ሰው፣ ሰውም አምላክ ሆኗልና ከኛ በነሳው ስጋም ወደ ሰማይ አረገ፡፡ ስለፍጹም የሰው ልጆች ፍቅር መድኃኔ ዓለም ተላልፎ ተሰጠ፡፡

በፊልጵ 2÷8 “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፣ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” ተብሎ እንደተጻፈው፡፡ በማዳኑ ስራ ውስጥ የቅድስት ድንግል ማርያም ድርሻ ታላቅ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በገላ 4÷4 “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ፡፡” ሲል ጽፏል፡፡

ዕለት ዕለት ፍቅሩን የከፈለልንን ዋጋ፣ ይህን መከራውንና ማዳኑን ዕለት ዕለት የሚያስቡ ገዳማውያን ሌሊትና ቀን በስግደትና በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቱን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጸና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: