ቼልሲ Vs ማንችስተር ዩናይትድ

- Advertisement -
Sidebar AD

የታላላቆቹ ፍልሚያ በስታምፎርድ ብሪጅ!

#Ethiopia | ​ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በመላው ዓለም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች አይን ወደ ለንደን፣ ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ያርፋል። ቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ ለክብር እና ለአራቱ ውስጥ የመቀመጥ ተስፋቸው ወሳኝ የሆነውን ፍልሚያ ያደርጋሉ።

​ የሁለቱ ቡድኖች ወቅታዊ ሁኔታ፦

​ቼልሲ (ሊያም ሮሲኒየር)፦
በሊጉ 6ኛ ደረጃ ላይ ቢገኝም፣ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች በደረሰበት ሽንፈት ጫና ውስጥ ነው። የዛሬው ሽንፈት ታሪካዊውን የሽንፈት ሰንሰለት እንዳይደግም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።

​ማንችስተር ዩናይትድ (ማይክል ካሪክ)፦
በ55 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባለፈው ሳምንት ከሊድስ የደረሰበትን አስደንጋጭ ሽንፈት ለመርሳትና ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ ሦስት ነጥብ የግድ ያስፈልገዋል።

​ የታሪክ ማህደር (Head-to-Head)፦

​ጠቅላላ ግንኙነት፦
198 ጊዜ ተገናኝተው ዩናይትድ 81 ጊዜ ሲያሸንፍ፣ ቼልሲ 56 ጊዜ ድል ቀንቶታል። 61 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

​የሜዳ ላይ የበላይነት፦
ዩናይትድ በስታምፎርድ ብሪጅ ካደረጋቸው ያለፉት 12 ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑ ለቼልሲ የሞራል የበላይነት ይሰጣል።

​ደርሶ መልስ፦
ዩናይትድ ዛሬ ካሸነፈ፣ ከ2019/20 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቼልሲን በደርሶ መልስ (Home & Away) ያሸነፈበት ዓመት ይሆናል።

​የማይሰለፉ ተጫዋቾች፦

​ቼልሲ፦
ሪስ ጄምስ፣ ሌቪ ኮልዊል እና ትሬቮ ቻሎባ (በጉዳት)

​ማንችስተር ዩናይትድ፦
ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ሃሪ ማጓየር (በቅጣት)፣ ሌኒ ዮሮ (በጉዳት)

​”በለንደን ሰማይ ስር ማን ይነግሳል?
ሰማያዊዎቹ ወይስ ቀያይ ሰይጣኖቹ?”
ግምታችሁን አጋሩኝ!

​#getu #PremierLeague #CHEmun #Chelsea #MUFC #StamfordBridge #MichaelCarrick #LiamRosenior #FootballEthiopia #EPLUpdate #ቼልሲ #ማንችስተርዩናይትድ #ፕሪሚየርሊግ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: