የአቡነ ሀብተ ማርያም ምልጃ እና ረድኤት አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ገዳም ስትገባ የተቀደሰ ልጅ እንደምትወልድ ተነግሯት የተመለሰችው እናቱ ዮስቲና ትባላለች። ልጅም ሲወልዱ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔርም አንጸው አሳደጉት።

በቤተ ክርስቲያንም የሰማውን “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የምትል ጸሎት እጅጉን ቢወዳት ሌሊቱን ሙሉ በቤቱ እየጸለያት የሚጋደል ሆነ። አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ ጓደኞቹን “ዝናም ይዘንማልና ወደቤት እንግባ” አላቸው። ቃሉን ሊሰሙት ባይወዱ በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ኃይለኛ ዝናም ዘነመ። ገና በአዳጊነት እድሜውም ብዙ ተአምራት ያደርግ ነበር፡፡

በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል። እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ ጌታችን ተገለጠለት። አቡነ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡

ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ ስለማንበቡ፣ ስለተጋድሎው፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። ከሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትንና ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የብርሃን ሠረገላም ሰጠው፣ መታሰቢያውን የሚያደርጉትን እንደሚምርለትም፣ ቃል ኪዳን ገባለት። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ስትለይም ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፤ ገዳማቸውን እንደግፍ ከበረከታቸውም እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: