”ትራምፕን የሚነዷቸው የእስራዔሉ ሰውዬ ናቸው”

- Advertisement -
Sidebar AD

ካማላ ሃሪስ

#Ethiopia | የቀድሞዋ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸውና ከኢራን ጋር በተቀሰቀሰው ግጭት ዙሪያ ክፉኛ ተቹ።

ሃሪስ በትራምፕ ላይ ያነጣጠረውን ይህን ትችት የሰነዘሩት በሚቺጋን ግዛት ዲትሮይት ውስጥ በተካሄደ የዴሞክራቲክ ፓርቲ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው።

በንግግራቸውም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ኢራኑ ጦርነት የገቡት በራሳቸው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ሳይሆን፣ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ግፊት “ተጎትተው” መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ጦርነት የአሜሪካ ህዝብ ፍላጎት የማይታይበትና የአገሪቱን ሰራዊት ለአላስፈላጊ አደጋ አሳልፎ የሰጠ መሆኑን ሃሪስ አክለው ገልጸዋል።

ካማላ ሃሪስ የትራምፕን አስተዳደር “ሙስና የሰፈነበትና ብቃት የሌለው” ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ ወታደራዊ እርምጃዎችን የሚወስዱት በሀገር ውስጥ ያሉባቸውን እንደ “ኤፕስታይን ፋይል” ያሉ ከባድ የፖለቲካ ውዝግቦች የህዝብ ትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር እንደሆነ በድፍረት ተናግረዋል።

የሃሪስ ንግግር ትራምፕ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ችላ ማለታቸውንና ዓለም አቀፍ ደንቦችን መጣሳቸውን እንደሚያሳይ የገለጹት የፖለቲካ ተንታኞች፣ ጉዳዩ በምርጫው ወቅት ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ገምተዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የቀረበባቸውን ውንጀላ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገዋል።

“ፕሬዝዳንት ትራምፕን ማንም ሊያዛቸው ወይም ሊገፋቸው አይችልም” ሲሉ ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ መሆኑን አመልክተዋል።

ይህ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው የቃላት ጦርነት የተካሄደው በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከረረበት እና የአሜሪካ የጥቅምት ወር የባለስልጣናት ምርጫ (Midterm Elections) በቀረበበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#menahriaFm #KamalaHarris #DonaldTrump #Netanyahu #USA #MiddleEast #Geopolitics #USPolitics #Election2026 #Ethiopia


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2