እንኳን ለዳግማዊ ትንሳኤ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ዳግማይ ትንሣኤ ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሑድ ደቀመዛሙርቱ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦ ትንሣኤው ፍጹም አማናዊ እንደሆነ ያሳየበት ዕለት ነው፡፡

በዮሐንስ 20÷24-30 እንደተጻፈው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ትንሣኤ ባለፈ የሚመጣውን እሑድ ሰይማ ታከብረዋለች፡፡ ጌታችን ለሐዋርያቱ ቀድሞ በተዘጋ ቤት ገብቶ ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ ተገልጦላቸው ነበር፡፡ ዳግመኛም ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ግን ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ጌታችንን በመካከላችን ተገልጦ አየነው ብለው ሲነግሩት የችንካሩን ምልክት በእጄ ካልዳሰስኩ አላምንም ብሎ ስለነበር ና ንካኝ ብሎታል፡፡ ቶማስ የተጠራጠረው በማቴዎስ 22÷23-33 እንደተገለጸው ትንሣኤ ሙታን የለም ብለው ከሚያምኑት ፈሪሳዊያን ወገን ስለነበረ ነው፡፡ የጌታችንን ጎን የነካች የቶማስ እጅ በኋላ ላይ ሳትበሰብስ በሕያውነት ለብዙ ዘመናት ኖራለች፡፡

በሀገረ ስብከቱና ሰማዕትነት በተቀበለባት በሕንድ ሀገር ከታቦት ጋር ከመንበሩ ላይ ያኖሯት ነበር፡፡ በዓመት በዓመት በእመቤታችን በዓል በአስተርዕ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች ዓመት አገልግሎ ያርፋል በዓመቱ ሊያጥን ሲገባ ትይዘዋለች እንዲህ እያለች ትኖራለች፡፡ ቶማስን “ና ጎኔን ንካ›” ሲለው በኋላ በዓለም ዞሮ ወንጌልን የሚሰብክ ነውና ሐዋርያ ከሆነ ዘንድ ደግሞ “ሐዋርያት እንዳሉት ጌታችን ተነስቷል” ብሎ ያስተምር ዘንድ አይገባውም ይልቁንም እንደ በ1ኛ ዮሐ1÷1-2 እንደተገለጸው “በጆሮአችን የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውንን የተመለከትነውን እጆቻችን የዳሰሱትን እንነግራችኋለን ሕይወት ለእኛ ተገልጻለችና አየናት” የሚል ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ነውና ቶማስን ና ንካኝ ብሎታል፡፡

አንድም የክርስቲያኖች ሰንበት የምንላት ዕለተ እሑድ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳባት በመሆኗ የእረፍት የመንግስተ ሰማይ አምሳል ብለን እናከብራታለን፡፡ የዕለቲቱን ክብርትነት፣ ዘወትር እሑድም ጌታችን የተነሳባትና ዳግሞ ትንሣኤውን የገለጠባት እንደሆነ እንድናስብ ለአክብሮተ ሰንበት ዳግሞ ተገለጠላቸው፡፡ አንድም በሉቃስ 24÷39 ጌታችን ራሱ የተገለጠበትን ዓላማ ሲነግራቸው “እጄን እግሬን እዩ ዳስሱኝም እኔ እንደሆንኩ ዕወቁ በእኔ እንደምታዩት ለምትሐት አጥንትና ሥጋ የለውምና እንዳላቸው የጌታችን ትንሳኤ ምትሐት ያይደለ አማናዊ በቀደመው ተዋሕዶ ባለመለወጥ እንደተነሳ ለማጠየቅ ተገለጠላቸው፡፡ ሲገለጥም በተዘጋ ቤት መግባቱ መለኮት አለመለየቱንና ወደ ሥጋ መለወጥ እንዳላገኘው ያስረዳል፡፡ ገዳማውያን ትንሣኤውን አምነው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ዓለምን ንቀው ይገዙለታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: