ኮንጎ ኢትዮጵያን ልትበልጥ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአይ ኤም ኤፍ (IMF) አዲስ ትንበያ መሠረት፣ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኢኮኖሚ በ2026 የኢትዮጵያን ደረጃ በመቅደም ከሰሃራ በታች አምስተኛው ግዙፍ ኢኮኖሚ እንደሚሆን ተገምቷል።

እንደ አይ ኤም ኤፍ ግምት፣ የኮንጎ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ( GDP) በዚህ ዓመት 123 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ አሃዝ ኢትዮጵያ ታስመዘግባለች ተብሎ ከሚጠበቀው 122 ቢሊዮን ዶላር በትንሹ ብልጫ በመውሰድ ደረጃዋን እንድታጣ ያደርጋታል።

ለዚህ የደረጃ ለውጥ ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች ተጠቅሰዋል፦

የኢትዮጵያ ብር ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ከፍተኛ ቅናሽ (Devaluation) ማሳየቱ በዶላር ሲሰላ የኢኮኖሚውን መጠን ዝቅ አድርጎታል። በአንፃሩ የኮንጎ ገንዘብ ከአሜሪካ ዶላር አንጻር የ25 በመቶ ጥንካሬ አሳይቷል።

ኮንጎ ለባትሪ ማምረቻነት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸውን እንደ ኮባልት እና መዳብ ያሉ ማዕድናትን በስፋት በማውጣትና ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት በመሳብ የኢኮኖሚ ጥንካሬዋን አሳድጋለች።

ምንም እንኳ የኮንጎ ኢኮኖሚ በጠቅላላ መጠን ቢቀድምም፣ የኢኮኖሚ እድገት ፍጥነትን በተመለከተ ግን ኢትዮጵያ አሁንም ቀዳሚ ናት።

| ኢትዮጵያ | 9.2% |
| ኮንጎ | 5.9% |

በአሁኑ ወቅት ከሰሃራ በታች አፍሪካ ቀዳሚዎቹን አራት የኢኮኖሚ ደረጃዎች የያዙት አገራት የሚከተሉት ናቸው፦

1. ደቡብ አፍሪካ
2. ናይጄሪያ
3. አንጎላ
4. ኬንያ

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#ቅዳሜገበያ #Etbusinessview #Ethiopia #EconomicNews #DRC #IMF #AfricaEconomy #BusinessUpdate


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: