#Ethiopia | ሃይንከን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘውን “ዴስፔራዶስ” የተሰኘ የቢራ ምርት በይፋ ለኢትዮጵያ ገበያ ማስተዋወቁን አስታወቀ።
ይህ ዛሬ የተዋወቀው አዲስ ምርት ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀ ታሪክ ያለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ50 በላይ በሚሆኑ የዓለም ሀገራት ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።
ኩባንያው ይህንን ምርት ማቅረቡ በሀገሪቱ ያለውን የፕሪሚየም ቢራ ገበያ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚያሸጋግረው ተገልጿል።
ዴስፔራዶስ የተለመደውን የቢራ አጠማመጥ ጥበብ ለየት ካለ ጣዕም ጋር በማዋሃድ አዲስ የቢራ ተሞክሮን ለተጠቃሚዎች የሚያስተዋውቅ ፈር ቀዳጅ መጠጥ ነው።
ምርቱ የላቁ የአልኮል መጠጦች ዋነኛ ግብዓት ተደርጎ በሚወሰደው በአጋቬ ጣዕም የተቀመመ ሲሆን ይህም ለየት ያለ የጣዕም ድብልቅ እንዲኖረው አስችሎታል። መጠጡ 5.9 በመቶ የአልኮል መጠን ያለው በመሆኑ በመደበኛ ቢራ እና በጠንካራ አልኮል መጠጦች መካከል አዲስ የጣዕም ድልድይ መፍጠር እንደቻለ ተመላክቷል።
የሃይንከን ኢትዮጵያ ይህ አዲስ እርምጃ የወጣቶች የመዝናኛ ምርጫ እየተለወጠ ከመምጣቱና አዳዲስ ነገሮችን የመፈለግ ዝንባሌ ከመጨመሩ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተጠቁሟል።
ምርቱ በተለይ ዘመናዊ የአኗኗር ዘዴን ለሚከተሉና ለየት ያለ አማራጭ ለሚሹ ወጣቶች ተስማሚ ተደርጎ ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም ኩባንያው ከአዳዲስ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር እንደ ‘አቬኒዳ ዴስፔራዶስ’ ያሉ ዓለም አቀፍ የመዝናኛ ተሞክሮዎችን ለኢትዮጵያውያን ተጠቃሚዎች ለማስተዋወቅ ማቀዱን ገልጿል።
ሃይንከን ኢትዮጵያ ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያተረፈ ብራንድ በሀገር ውስጥ ማምረት መጀመሩ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ያለውን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።
ድርጅቱ የምርቱን ጥራት በጠበቀ መልኩ ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረቡ ለዘርፉ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውና የተጠቃሚዎችን ፍላጎት ለማሟላት ያለውን ስትራቴጂያዊ ቁርጠኝነት በተግባር እንደሚያሳይ ተገልጿል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ


Source: GetuTemesgen









No comments yet.