#Ethiopia | በማሌዥያ ሰባህ ግዛት፣ ሳንዳካን ከተማ ውስጥ በደረሰ ከባድ የእሳት አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ አልባ መሆናቸው ተሰምቷል።
አደጋውን አስመልክቶ የወጡ መረጃዎችን እንደሚከተለው አቀናጅተነዋል።
በሳንዳካን ግዛት በምትገኘው ሰባህ መንደር የተከሰተው ይህ ድንገተኛ የእሳት አደጋ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ መኖሪያ መንደሩ በመስፋፋቱ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።
200 የሚጠጉ የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ በእሳቱ ወድመዋል።445 የሚጠጉ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል።
የእሳቱ መነሻ እስካሁን በግልጽ እንዳልታወቀና በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
የእሳት አደጋ ተከላካዮች እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም፣ የሚከተሉት ሁለት ነጥቦች አደጋው የከፋ እንዲሆን አድርገውታል።
1. በአካባቢው የነበረው ጠንካራ ነፋስ እሳቱ ከአንድ ቤት ወደ ሌላው በፍጥነት እንዲሸጋገር ረድቷል።
2.ቤቶቹ በጣም ተቀራርበው የተገነቡ መሆናቸው ለእሳቱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
በአሁኑ ወቅት ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ማሌዥያ #የእሳትአደጋ #ሳንዳካን #ሰባህ #ዜና #Malaysia #Sandakan #FireAccident
Source: GetuTemesgen









No comments yet.