ትራምፕ ለኢራን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች ሲሉ በጽኑ ከሰሱ።

ትራምፕ “ከእንግዲህ ደግ መሆን አብቅቷል” በማለት ኢራን ድርድሩን ካልተቀበለች እጅግ ከባድ ዋጋ እንደምትከፍል ዝተዋል።

​ኢራን ትናንት የከፈተችው ተኩስ በአሜሪካና በኢራን መካከል የተደረሰውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ የጣሰ ነው ብለዋል።

​ድርድሩ ካልተሳካ አሜሪካ በኢራን ውስጥ የሚገኙ እያንዳንዱን የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎችና ድልድዮች እንደምታወድም አስጠንቅቀዋል።

ነገ ሰኞ የአሜሪካ ተወካዮች ከኢራን ጋር ለመደራደር ወደ ፓኪስታን፣ ኢስላማባድ ያመራሉ።

“ለ47 ዓመታት በሌሎች ፕሬዝዳንቶች ሳይደረግ የቆየውን እርምጃ በእኔ ዘመን መፈጸም ለእኔ ክብር ነው” ሲሉ ትራምፕ በቁጣ ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ ተንታኞች የሰኞው ድርድር ካልተሳካ ቀጠናው ወደ መጠነ ሰፊ ጦርነት ሊገባ እንደሚችል ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። ትራምፕ “በፈጣንና በቀላል ሁኔታ ይወድማሉ” ማለታቸው በዲፕሎማሲው ዓለም ትልቅ ድንጋጤ ፈጥሯል።

​ሰላም ወይስ መጠነ ሰፊ ጦርነት? የሰኞው ድርድር የዓለምን እጣ ፈንታ ይወስናል።

​#getu #Trump #IranConflict #IslamabadSummit #HormuzStrait #BreakingNews #WorldPolitics #MilitaryTension #ትራምፕ #ኢራን #ሰበርዜና #መካከለኛው ምስራቅ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2