የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው የ46.7 ሚሊየን ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከሀገሪቱ የሕዝብ ስብጥር አንፃር ሲመዘን ትልቅ የጥያቄ ምልክት የሚያስነሳ ነው።
ቁጥሮቹን በዝርዝር ስናነፃፅራቸው የሚከተሉትን እውነታዎች እናገኛለን
1. የአዋቂ እና የሕፃናት ቁጥር ንፅፅር
በዓለም ባንክ እና በስታቲስቲክስ መረጃዎች መሠረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 130 ሚሊየን አካባቢ እንደሆነ ይገመታል። ከዚህ ውስጥ
41% የሚሆነው (53.3 ሚሊየን) ዕድሜው ከ15 ዓመት በታች ነው።
ለምርጫ ብቁ ለመሆን ግን 18 ዓመት መሙላት ግድ ይላል ከ15 እስከ 18 ዓመት ያለውን የዕድሜ ክልል ስንቀንስ ድምፅ ለመስጠት ብቁ የሆነው ሕዝብ ከ 60 እስከ 65 ሚሊየን አይበልጥም።
ሪፖርቱ እንደሚለው 46.7 ሚሊየን ሰው ተመዝግቧል ካልን በሀገሪቱ ካለው አዋቂ ሕዝብ ውስጥ 75% የሚሆነው ተመዝግቧል ማለት ነው።
ይህ በፀጥታ እና በመሰረተ ልማት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች እንዴት ሊሳካ ቻለ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው።
2. የዲጂታል ምዝገባው እና ነባራዊ ሁኔታው
ማስታወቂያው በኦንላይን እና በሞባይል መተግበሪያ መመዝገብ እንደሚቻል ይጠቅሳል ሆኖም
በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር ከጠቅላላው ሕዝብ 25% አካባቢ ብቻ ነው።
አብዛኛው የገጠር ሕዝብ ስማርት ፎን እና የተረጋጋ የኢንተርኔት አገልግሎት በሌለበት ሁኔታ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በዲጂታል መንገድ ተመዝግቧል ማለት የቁጥር ጋጋታ እንጂ እውነታ አይመስልም።
3. ከቀድሞ ምርጫዎች ጋር ያለው ንፅፅር
በ2013ቱ (6ኛው) አገራዊ ምርጫ ወቅት ተመዝጋቢው ሕዝብ 38 ሚሊየን አካባቢ ነበር።
አሁን በተጠቀሰው አጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥሩ ወደ 46.7 ሚሊየንማደጉ ካለፈው ምርጫ በ8.7 ሚሊየን (ወይም በ23%)ብልጫ አለው ማለት ነው።
ይህ እድገት ከሀገሪቱ የሕዝብ እድገት ምጣኔ በላይ ሆኖ መገኘቱ መረጃው የተጋነነ መሆኑን ይጠቁማል።
በሪፖርቱ ላይ የሰፈሩት ቁጥሮች (ለምሳሌ 25.2 ሚሊየን ወንዶች እና 21.5 ሚሊየን ሴቶች) በጣም ዝርዝር ቢመስሉም ከሀገሪቱ የዕድሜ ስብጥር እና ነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀሩ ግን እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ናቸው።
ይህም መረጃው ከእውነተኛ የምዝገባ ሂደት ይልቅ ቁጥሮችን በማጋነን ሕዝባዊ ተሳትፎው ከፍተኛ ለማስመሰል የሚደረግ ጥረት ይመስላል ምን ትላላችሁ ?
እስኪ ሃሳብ አስተያይታችሁን በጨዋነት አካፍሉን
Source: Yeneta Tube









No comments yet.