የውጭ ምንዛሪ ያድናል የተባለለት የሴራሚክ ምርት ለገበያ ሊቀርቡ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia |​ ይህ የተገለፀው ኢትዮደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በ”Golden Tier Level” የምርት አከፋፋይነት ደረጃ ከባይጃይ ሴራሚክ ማምረቻ ኢንዱስትሪ (ቱለፋ ሴራሚክ) የካቲት 27፣ 2018 ዓ.ም. ጋር ያደረጉትን የሴራሚክ ውጤቶችን የማከፋፈል ስምምነት ምክንያት በማድረግ በተካሄደ የማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው።

ሥነ ሥርዓቱ ታላላቅ እንግዶች በታደሙበት ሚያዝያ 10 2018 ዓ.ም በሎፍት አፓርትመንት ሆቴል ተካሂዷል።

የሁለቱ ድርጅቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በተገኙበት የማብሰሪያ ሥነ-ሥርዓቱ የተካሄደ ሲሆን የተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎችም ንግግር አድርገዋል።

በማብሰሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተገለፀው የኢትዮጵያን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ለማገዝ እንዲሁም ጥራት ያላቸውን የቤት ውስጥ ማጠናቀቂያ ምርቶች ለደንበኞች በተሻለ ተደራሽነት ለማቅረብ ስምምነቱ አይንከፋች ይሆናል ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ሥራዎች በአገሪቱ እየተስፋፉ መምጣታቸውን በዕለቱ የተገለፀ ሲሆን መንግሥትም ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት በተለይ በአገር ውስጥ የሚመረቱ እቃዎችን ለደንበኞች በማቅረብ የውጭ ምንዛሪን ማዳን ሁነኛ አማራጭ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ጥራት የሚመረቱ የባይጃይ ሴራሚክ ውጤቶች( ቱለፋ ሴራሚክስ) በኢትዮደር ሰፊ የማከፋፈል መረብ አማካይነት ለገበያ እንዲቀርቡ ለማድረግ ያለመ መሆኑም በተሰጠው መግለጫ ተጠቅሷል።

ይህ በጋራ የተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት የሀገር ውስጥ ምርትን የማበረታታት፣ የውጭ ምንዛሬን በመቆጠብ እና ለኮንስትራክሽን ግብዓቶች የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ተገልጿል።

በዕለቱም ከመጀመሪያዎቹ የምርቱ ተጠቃሚ የኮንስትራክሽን ፕሮጄክት ባለቤቶች ጋር እና ቀዳሚ ሁለተኛ ደረጃ አከፋፋዮች ጋር የመግባቢያ ሠነዶች ተፈርመዋል።

የማብሰሪያ ሥነ -ሥርዓቱ ላይ እንደተወሳው ለኮንስትራክሽን ዘርፉ የሚሆኑ ግብአቶችን አገር ውስጥ አምርቶ አገር ውስጥ በመሸጥ በየጊዜው እያደገ ለመጣው የአገሪቱ የግንባታ ሥራ ትልቅ ክፍተት እንደሚሞላ ተነግሯል።

ከአዲስ አበባ በ65 ኪ.ሜ ርቀት በሚገኝ ቱለፋ በተባለ ቦታ የሚገኘው የባይጂያ ፋብሪካ፣ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በሚበልጥ ኢንቨስትመንት የተገነባ ሲሆን፣ በዓመት 14 ሚሊዮን ካሬ ሜትር የሚሸፍኑ የሴራሚክ ምርቶችን የማምረት አቅም አለው።

ይህም ፋብሪካውን በኢትዮጵያ ግዙፉ የሴራሚክ አምራች ድርጅት ያደርገዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1