“በሃላንድ ቦታ ሆኜ ከሳሊባ እና ጋብሬል ጋር ከመጋፈጥ መጽሐፍ ማንበብ እመርጣለሁ” — ፔፕ ጋርዲዮላ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የማንችስተር ሲቲው ስትራቴጂስት ፔፕ ጋርዲዮላ አርሰናልን መግጠም ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነና መድፈኞቹ አሁንም ለዋንጫው ያላቸውን የበላይነት ገለጹ። ጋርዲዮላ የአርሰናልን ወቅታዊ ጥንካሬ ሲያደንቁ “አሁንም ቢሆን የሊጉ መሪ አርሰናል ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

​የመድፈኞቹን የኋላ ክፍል ጥንካሬ በተመለከተም ጋርዲዮላ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፦

​”ከጋብሬል እና ሳሊባ ጋር መፋለም እጅግ ከባድ ነገር ነው። እውነት ለመናገር በሃላንድ ቦታ ሆኜ ከእነሱ ጋር ከመታገል ይልቅ ቁጭ ብዬ መጽሐፍ ማንበብን እመርጣለሁ።”

​አሰልጣኙ አክለውም አርሰናል እጅግ ድንቅ ቡድን እንደሆነና እነሱን መግጠም አድካሚ መሆኑን ጠቁመው፣ ምንም እንኳን መድፈኞቹ በግብ ክፍያም ሆነ በነጥብ መሪነቱን ቢይዙም ሲቲዎች አሁንም ለዋንጫው ያላቸው ተስፋ እንዳልተሟጠጠ ገልጸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#Arsenal #ManCity #PepGuardiola #PremierLeague #Saliba #Gabriel #Haaland #FootballNews #EPL


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2