#FastMereja I በኢትዮጵያ የካንሰር መከላከልና እንክብካቤ ሥራ ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት ያለመው “ብሬቭኸርትስ የኢትዮጵያ ካንሰር ፋውንዴሽን” (BraveHearts of Ethiopia Cancer Foundation) ተመሰረተ። ፋውንዴሽኑ በሀገሪቱ ያለውን የካንሰር መከላከል አቅም በማጠናከር፣ ግንዛቤ በመፍጠርና ሀብት በማሰባሰብ የሕሙማንን ሕይወት ለመታደግ እንደሚሠራ አስታውቋል።
የፋውንዴሽኑ መሥራች ወይዘሮ ሌሊሴ ዱጋ በምረቃው ወቅት እንደገለጹት፣ ተቋሙ በኢትዮጵያ በካንሰር በሽታ ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ቆርጦ ተነስቷል። ፋውንዴሽኑ በዋናነት ጠንካራ አጋርነቶችን በመፍጠር፣ ተደራሽነትን በማስፋት እና ለሕሙማን የሚደረገውን ድጋፍ በማሳደግ ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።


Source: FastMereja








No comments yet.