ህወሓት ውሳኔው ሌላ ዙር ጦርነት የማያውልድ መሆኑ በደንብ ማጤን ይገባዋል! ”
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ዛሬ ከሰዓት የሰጡትን መግለጫ ታድሟል።
መግለጫው በቀናት በፊት ህወሓት በአክሱም ከተማ በ2013 ዓ.ም የተመረጠው መንግስት እንዲመለስ መወሰኑና እንድምታው እንዲሁም የፌደራል መንግስት ማድረግ ስላለበትና ስለራሳቸው ቀጣይ ሁኔታ ያተኮረ ነበር።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?
የትግራይ አሁናዊ የፖለቲካ ሁኔታ ፦
” ትግራይ ከጦርነቱ በፊት የተሻለ የፓለቲካ ቁመናና የህዝብ አንድነት ነበራት ” ያሉት ፕሬዜዳንቱ ” በጦርነቱ ጊዜም እንዲሁ ህዝብና የፓለቲካ ሃይሉ በአንድነት በመሆን የመከላከል ወግያ አካሂደዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።
አስከፊው እና ደም አፋሳሹ የትግራዩ ጦርነት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከቆመ በኋላ በክልሉ የፓለቲካ ሃይሎች ከፍተኛ መከፋፈል መከሰቱን፤ መከፋፈሉ ተከትሎ ትልቅ የሆነ ጦርነትና የፓለቲካ መተራመስ የወለደው ቀውስ መፈጠሩን ገልጸዋል።
” መከፋፈሉና ቀውሱ የትግራይ የመደራደር አቅም እያዳከመ የፌደራል መንግስት የመፈፅም ተነሳሽነት ጉድለት ታክሎበት ተፈናቃዮች ወደቄያቸው አልተመለሱም፤ የክልሉ ግዛታዊ አንድነት አልተረጋገጠም ” ብለዋል።
የህወሓት የሰሞኑ የአክሱም ውሳኔ ፦
ህወሓት ሚያዝያ 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከታጣቂ ከፍተኛ አመራሮች ባካሄደው ስብሰባ ” 2.8 ሚሊዮን ህዝብ የመረጠው መንግስታዊ አስተዳደር እንዲመለስ ” ወሰኗል ።
” ይመለስ ” የተባለው መንግስታዊ አስተዳደር ጳጉሜን 2012 ዓ.ም በተካሄደና ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያልተቀበለው ምርጫ የተቋቋመ ሲሆን ፤ በኋላም የትግራዩ ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ከሆኑት አንዱ ነው።
ሌ/ጄነራል ታደሰ ” ህወሓት ያለፈውን መንግስት ወደ ስልጣኑ እንዲመለስ መወሰኑ እንድምታው አወንታዊ ነው አሉታዊ ? እንዳለፉት ዓመታት ሌላ መከፋፈል የሚፈጥር ነው ወይስ አንድነት የሚያመጣ ? ውሳኔው ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚጣረስና ከፌደራል መንግስት ሌላ ዙር ግጭት እንዳያዋለድ በማስተዋልና በጥልቀት መጤን አለበት ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
” ትግራይ ጦርነቱን ተከትሎ በፓለቲከኞቿ መካከል በተፈጠረው መከፋፈል ተዳክማለች ሌላ ጦርነት የሚሸከም አቅምና ብቃት የላትም ፤ ስለሆነም ህወሓት እነዚህንና ሌሎች ውሳኔውን ተከትለው የሚመጡ መዘዞች ቀድሞ ማስተዋል ይጠበቅበታል ” ብለዋል።
” የህወሓት ውሳኔ በክልሉ ሌላ መከፋፈልና ተጨማሪ ግጭትና ጦርነት የማይጋብዝ ከሆነ ፤ ለህዝብ በችግር ላይ ችግር የማይጭን ከሆነ የሚከበር ነው የሚሆነው ” ሲሉ አክለዋል።
በፌደራል መንግስት መደረግ ስለበት፦
” የፌደራል መንግስት የፕሪቶሪያ ስምምነት ፈራሚ አካል ነው ፤ ስለሆነም በትግራይ ያለውን የፓለቲካ ቀውስ የሚያረግቡ ስራዎችን መስራትና ማገዝ አለበት ” ሲሉ ሌ/ጄ ታደሰ ወረዳ ተናግረዋል።
” ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲረጋገጥ ፣ የትግራይ መልሶ ግንባታ እንዲካሄድ ማድረግ የፌደራል መንግስት በፕሪቶሪያ ውል የፈረመባቸው ነጥቦች መፈፀም አለበት ” ብለዋል።
” ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ሳይመለሱ ፤ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ሳይረጋገጥ 6 ኛ ክረምት እየመጣ ነው ፤ በዛ ላይ የመንግስት ደመወዝ ፣ የክልሉ በጀት ማቋረጥና ነዳጅ መከልከልና ሌሎች ችግሮች መፈታት አለባቸው ” ሲሉ ተደምጠዋል።
” የፌደራል መንግስት በትግራይ ያለውን ፓለቲካዊ ከመፍታት ይልቅ በማወሳሰብ ገፊ ግጭትና ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ መስራት ይጠበቅበታል ” ብለዋል።
የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መከልከል፦
ሌ/ጄነራል ታደሰ ” የልማት በጀት ማቆም ፣ ነዳጅ መከልከል ማለት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ያቋቋምከው ጊዚያዊ አስተዳደር እንደማፍረስ የሚቆጠር ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስለ ራሳቸው ቀጣይነት ፦
ፕሬዜዳንቱ በመግለጫቸው እንደገለፁት አንደኛ ዙር የስልጣን ጊዚያቸው ከማብቃቱ ከሁለት ወራት በፊት የተሻለ መፍትሄ (መፍትሄ ያሉትን በመግለጫቸው አልጠቀሱትም) ክልሉ ለሚመራ ከፍተኛ ካውንስል ማቅረባቸውንና አጀንዳ ይዞ የሚያደምጣቸው እንዳልተገኘ ተናግረዋል።
ህወሓት ሰሞኑን የወሰነው ያለፈው መንግስት ይመለስ ጥሪ ለክልሉ ህዝብ የሚበጅ ፤ ሌላ ግጭት የማይጋብዝ ከሆነ የፓርቲው ውሳኔ በመሆኑ ብዙ እንደማይከፉበት አብራርተዋል።
በውሸት፣ በማጥቆር፣ በመፈረጅና ‘ጠላት ነው ‘ በሚል ቅስቀሳና የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ ከስልጣናቸው ማውረድ እንደማይበጅና እንደማይታሰብ በአፅንኦት የተናገሩት ፕሬዜዳንቱ ” ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ዝግጁ ” መሆናቸውን አመላክተዋል።
ነገር ግን ጊዜያዊ አስተዳደሩ አሁንም ስራ ላይ እንደሆነ፣ ካቢኔው የዕለት ተዕለት ስራውን እንደሚቀጥል ፤ ማንኛውም የመንግሥት ሰራተኛ ተገልጋዮችን ለማገልገል በስራ ገበታው ላይ መገኘት እንዳለበት አሳስበዋል።
” መንግሥት የሌለ የሚመስል እንቅስቃሴ መቆም እንዳለበት ” አስጠንቅቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.