በሰይፉ ፋንታሁን እና በወዳጆቹ እንቅልፍ አልባ ለሊቶች የተገኘ በረከት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታዋቂው የሚዲያ ሰው የቴሌቪዥን ሾው አቅራቢ ሰይፉ ፋንታሁን፣ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ሲያከናውን የቆየው መጠነ ሰፊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ በስኬት ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ለበርካታ ለሊቶች ሰይፉ እና ወዳጆቹ እንቅልፍ አጥተው ሲያስተባብሩት የነበረው መርሃ ግብር ፍሬ አፍርቶ፣ ለግዙፉ ህንፃ ማጠናቀቂያ የሚውሉ የህንፃ መገንቢያ ቁሳቁሶች ዛሬ ወደ ማዕከሉ ግቢ ገብተዋል።

​ወደ ማዕከሉ የገቡት ግብዓቶች
በዋናነት፦​የሴራሚክስ ውጤቶች ፤​ልዩ ልዩ የህንፃ ማጠናቀቂያ ቁሳቁሶች እና ​ሌሎች መሠረታዊ የግንባታ ግብዓቶች ናቸው።

​ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው በሰይፉ ፋንታሁን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜትና በፅናት ላደረገው ጥረት፣ ለጋስ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሰጡት ፈጣንና ልባዊ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል።

ሰይፉ ለወገኖቹ መጠለያ እንዲሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ያደረገው እንቅስቃሴ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፎለታል።

​የእነዚህ ቁሳቁሶች ወደ ማዕከሉ መግባት፣ እየተገነባ ያለው ግዙፍ ህንፃ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ትልቅ አቅም ይፈጥራል። ግንባታው ቶሎ መጠናቀቁ ደግሞ፦

​በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ አረጋውያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን መጠለያ የማግኘት ተስፋ ያፋጥናል፤​ማዕከሉ ለተጨማሪ ወገኖች እርዳታ እንዲያደርግ የቦታ ጥበቱን ይቀርፋል፤​የዜጎችን የመረዳዳት ባህል ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል።

​አሁንም ቀሪ የግንባታው ሂደት ተፋጥኖ የብዙዎችን መጠለያ የመሆን ተስፋው እውን እንዲሆን ሁለተኛው ዙር የገቢ ማሠባሠቢያ ሂደቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

https://youtube.com/@mekedonia?si=eYN5USIcNC86EgB8

​Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1