ታላቅ ዜና🎉🎉🎉
በታዝማ የውስጥ ደዌና የቀዶ ሕክምና ልዩ ማዕከል የተዘጋጀው 4ተኛው ዙር ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና በዶ/ር ፍቅሩ ማሩ መታሰቢያነት በወራቤ ከተማ ተዘጋጀ
በሀገራችን የልብ ህክምናው መስክ ጉልህ ሚና የተጫወቱ የሀገር ባለውለታ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን መታሰቢያ በማድረግ በኢትዮጵያ የሕፃናትና የአዋቂዎች የልብ ቀዶ ሕክምና ፈር ቀዳጅ የሆነው ፣ “ዝምተኛው ጀግና” በሚል የሚታወቀውና ሁሌም በህክምናው ዘርፍ ያስመዘገባቸው ስኬቶች በሚነገርለት ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ሕክምና ልዩ ማዕከል ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ባለሙያዎቹን እና ለዓመታት በተግባር የተፍተነ ልምድን በመጠቀም ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ ከሚያዝያ 13 – 17 ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና በወራቤ ከተማ ሊያካሄድ ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።
የማዕከሉ ተወካይ እንደገለጹት “ይህ ዘመቻ ላለፉት 15 ዓመታት አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የልብ ሕክምናን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማድረስ በነበረው ጉዞ እምነት ለጣለብን ማኅበረሰብ ውለታ የምንመልስበት ነው” ያሉ ሲሆን እንዲህ ያለ ውስብስብ ሕክምና በሀገር ውስጥ በራስ አቅም መስጠትም ትልቅ ኩራት መሆኑን ገልጸዋል።
ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ የሕክምና አገልግሎት ከዚህ ቀደም በጅማ፤ በጅግጅጋ እና በሀዋሳ ከተማዎቸ ላይ በስኬት የተከናወነ እና በርካቶችም የዚህ ነፃ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን ይህንን ትልቅ ወጪ ና ግብአትን የሚጠይቅ ተልእኮ በሀገር ውስጥ በራስ አቅም እንዲሰጥ ማድረግ ለሀገራችን ትልቅ ተስፍ ነው።
የታካሚዎችን ቀዶ ሕክምና ሂደት በታዝማ ማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ይከታተሉ
ለበለጠ መረጃ
☎️ 0954886225 / 9893.
📍ጎተራ ኮንዶሚኒየም አዲስ አበባ
Source: FastMereja









No comments yet.