አንዳንድ ሰዎች ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ሲጓጓዙ ለጉዞው ፈጽሞ የማያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ የመሰብሰብና ሻንጣዎችን የማብዛት ልማድ አለባቸው፡፡ እነዚህ ሻንጣዎች ግን ከሸክም ውጪ ምንም ትርፍና ጥቅም የላቸውም፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ አንዳንደ ጊዜ በሕይወት ጉዟችን ላይ አላስፈላጊ ሸንጣዎችን (Extra luggage) ተሸክመን እንኖራለን፡፡ እነዚህ አላስፈላጊ ሻንጣዎች በሕይወታችን ላይ ጫና ከማስከተልና ጉዟችንን አድካሚ ከማድረግ ሌላ ምንም ጥቅም የላቸውም፡፡
አንዳንዶቹን ከነመፍትሄያቸው እንመልከት፡፡
1. የስሜት ሸንጣ
የስሜት ሻንጣ የሚወክለው ያለፈ ጉዳት፣ ቂምና ጥላቻ፣ መራራነት፣ ጸጸትና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ይህንን ሻንጣ ለማራገፍ፡-
• ሰዎችን ይቅር በማለት ውስጥን ነጻ ማድረግ፡፡
• ያለፈው ታሪክን ከዛሬ ማንነት ጋር አለማነካካት፡፡
• ካለፈው መማር፣ ለነገ ማቀድ፡፡
2. የአእምሮ ሸንጣ
የአእምሮ ሻንጣ የሚወክለው አሉታዊ ሃሳቦችን፣ ፍርሃትን፣ ጥርጣሬን፣ የተገደበና የአልችልም አመለካከትንና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ይህንን ሻንጣ ለማራገፍ፡-
• ምንም ማስረጃ የሌላቸውንና ተጨባጭ ያለሆኑ ሃሳቦችን በትክክለኛ ማስረጃ በመሞገት ከውስጥ ማውጣት፡፡
• “አልችልም” እና “አይሳካልኝ” መሰል ሃሳቦችን በአዎንታዎዎቹ መቀየር፡፡
• መሰልጠን፣ ማንበብ፣ ማሕበራዊ ሚዲያዎች በጥንቃቄ መምረጥ፡፡
3. የግንኙነት ሻንጣ
የግንኙነት ሻንጣ የሚወክለው መርዛማ ባህሪይ ያለው ወደጅነቶች፣ ካለልክ በሰው ላይ መጣበቅ፣ ያልተፈቱ ግጭቶችና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ይህንን ሻንጣ ለማራገፍ፡-
• ለሰዎች የቀይ መስመርን ማበጀትና አስፈለጊ ክልከላዎችን ማድረግ፡፡
• ከሰዎች ጋር ያለ ተቃርኖን በሰላማዊ መንገድና በንግግር መፍታት፡፡
• ለህልውናችን አስጊ የሆኑ ግንኑነቶችን ጓደኝነቶችን ማቋረጥ፡፡
4. የልማድ ሻንጣ
የልማድ ሻንጣ የሚወክለው አጉል ሱሶችም፣ የተዘባረቀ የአኗኗር ዘይቤን፣ የመወላወልና የግድ የለሽነት ልምምዶችንና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ይህንን ሻንጣ ለማራገፍ፡-
• መጥፎ ልማዶችን በትክክለኛና በጤናማ ልማዶች የመቀየርን ስራ መጀመር፡፡
• በጥቂቱ ጀምሮ ባለማቆም ራስን ማሻሻል፡፡
• አጉል ልማዶችን የሚያስታውሱና የሚያነሳሱ ሰዎችና ሁኔታዎችን መራቅ፡፡
5. የቁሳ-ቁስ ሻንጣ
የቁሳ-ቁስ ሻንጣ የሚወክለው የማንጠቀምባቸውን ነገሮች መሰብሰብ፣ ለታይታ መኖር፣ ለሆነውም ላልሆነውም ገንዘብ መበደርና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ይህንን ሻንጣ ለማራገፍ፡-
• ትኩረታችንን ከምንፈልጋቸው ነገሮች ላይ መለስ በማድረግ ወደሚስፈልገን ነገር ላይ ማተኮር፡፡
• ከገቢያችን ጋር የተመጣጠነ ሕይወት መኖር፡፡
• ጥቅም የሌላቸውን ወይም አናሳ የሆነ ጥቅም ያላቸውን ነገሮች አለመሰብሰብ፣ ያሉትንም ማስወገድ፡፡
6. የሃላፊነት ሻንጣ
የሃላፊነት ሻንጣ የሚወክለው የሰዎችን ሸክምና ሃላፊነት ካለአግባብ መሸከም፣ ሰዎችን ሁሉ የማስደሰት ትግል፣ ሰዎች በእኛ ላይ ስላላቸው አመለካከት ካለልክ መጨነቅና ለማስተካከል መታገል እና የመሳሰሉትን ነው፡፡ ይህንን ሻንጣ ለማራገፍ፡-
• ሰዎች የራሳቸው አመለካከት እንዳላቸውና እሱም እኛን እንደማይወክል አምኖ መቀበል፡፡
• ሰዎችን ሁሉ መርዳትና ካሉበት ማውጣት እንደሌለብንና እንደማንችልም አምኖ መቀበል፡፡
• መጀመሪያ ራሳችንን ማሻሻልና መለወጥ እንዳለብን በማመን እሱ ላይ መስራት፡፡
LIKE & SHARE !!!
Source: GetuTemesgen









No comments yet.