#Ethiopia | በናይጄሪያ የንግድ ከተማ ሌጎስ፣ የከብት ዋጋ ከመቼውም ጊዜ በላይ በመናሩ ምክንያት አንድን ትልቅ በሬ ለመግዛት የሚጠየቀው ገንዘብ አንዳንድ ያገለገሉ መኪናዎችን መግዛት ከሚያስችለው ዋጋ ጋር እኩል መሆኑ ተሰምቷል። ይህ ክስተት በከተማዋ ስጋ ሻጮችና ሸማቾች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ገበያ የአንድ ትልቅ በሬ ዋጋ እስከ 2.5 ሚሊዮን ናይጄሪያ ናይራ (1,613 ዶላር) ደርሷል። ይህ አሀዝ በናይጄሪያ ‘ቶኩንቦ’ ተብለው ከሚጠሩት ያገለገሉ ሚኒባሶችና ትናንሽ የቤት መኪናዎች መሸጫ ዋጋ ጋር የሚመጣጠን አልፎም የሚበልጥ ሆኖ ተመዝግቧል።
የሌጎስ ስጋ ሻጮች ማህበር እንደገለጸው፣ ቀደም ሲል በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ናይራ ብቻ ይሸጡ የነበሩ ከብቶች፣ አሁን ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መጠየቃቸው ስጋን እንደ ቅንጦት እቃ እያስቆጠረው ነው።
በከብት አርቢዎችና በግብርናው ዘርፍ ላይ ያለው አለመረጋጋት በከብት አቅርቦት ላይ ትልቅ እጥረት ፈጥሯል።ለዚህ በምክንያትነት የተጠቀሰው
-ከብቶችን ከእርባታ ቦታዎች ወደ ሌጎስ ገበያ ለማጓጓዝ የሚወጣው የትራንስፖርት ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ።
-ችግሩን ይቀርፋሉ ተብለው የታቀዱ የከብት እርባታና የግብርና ፕሮጀክቶች በታሰበላቸው ፍጥነት አለመከናወናቸው ሲሆን ይህ አስገራሚ የዋጋ ፉክክር በናይጄሪያ ያለውን የኑሮ ውድነትና የኢኮኖሚ ጫና በግልጽ የሚያሳይ ሆኗል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#አስገራሚዜና #ናይጄሪያ #ሌጎስ #የኑሮውድነት #የገበያዋጋ #አፍሪካ #NigeriaEconomy #lagosmarketing
Source: GetuTemesgen









No comments yet.