“በሆርሙዝ ለተፈጠረው ቀውስ ሁለቱም ተጠያቂ ናቸው” ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ ላይ እየታየ ላለው ከፍተኛ ውጥረት አሜሪካና ኢራን እኩል ተጠያቂ መሆናቸውን ገለጹ። ፕሬዝደንቱ ሁለቱም ሀገራት ከገቡበት የ”እልህ መጋባት” መንፈስ ወጥተው ወደ ውይይት እንዲመለሱም ጥሪ አቅርበዋል።

​ፕሬዝደንት ማክሮን በሰጡት መግለጫ ያሰፈሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

​በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ ለሚታየው ተደጋጋሚ መከፈትና መዘጋት ዋነኛው ምክንያት ሁለቱ ሀገራት እርስ በርሱ የሚጋጭ ውሳኔ ማሳለፋቸውና ለዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው ብለዋል።

የሄዝቦላህና እስራኤል የሰላም ስምምነት እንዲሁም በኢዝላማባድ የተጀመረው ድርድር ለሆርሙዝ ሰርጥ ሰላም “በረከት” ይሆናል ተብሎ ቢጠበቅም፤ በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና በኢራን መካከል ያለው ፍጥጫ ሂደቱን እንዳደናቀፈው ማክሮን ጠቁመዋል።

በደቡባዊ ሊባኖስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የነበሩ የፈረንሳይ ወታደሮች መገደላቸውንና መቁሰላቸውን ያስታወሱት ፕሬዝደንቱ፤ ለጥቃቱ ሄዝቦላህን ተጠያቂ አድርገዋል። የጦርነቱ መራዘምም ለዚህ መሰሉ ሰብዓዊ ቀውስ መንስኤ መሆኑን አክለዋል።

​ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በማጠቃለያቸው፤ ቀጠናው ወደ ከፋ ግጭት ውስጥ ከመግባቱ በፊት ሁለቱም ኃይሎች ቆም ብለው እንዲያስቡና ለዓለም አቀፉ መረጋጋት ሲሉ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ ንግግር እንዲመለሱ አሳስበዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#EmmanuelMacron #HormuzStrait #USA #Iran #France24 #GlobalPeace #Lebanon #InternationalNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: