በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ የበልግ ዝናብ እንደሚቀጥል ተገለጸበተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የጀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ የበልግ ዝናብ እንደሚቀጥል ተገለጸ
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የጀመረው የበልግ ዝናብ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ሆኖ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቋል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ የታየው የበልግ ዝናብ ስርጭቱና መጠኑ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢንስቲትዩቱ የትንበያና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ተናግረዋል።
በተለይም በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እየዘነበ መሆኑን ያስታወቁት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ዝናቡ ለግብርና ሥራና ለውኃ አቅርቦት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ቢሆንም፣ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ገልጸዋል። ባለፉት ቀናት ከ60 በሚበልጡ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከ30 እስከ 148 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ከባድ ዝናብ መመዝገቡን ዶክተር አሳምነው ጠቅሰው፤ የዝናብ ሁኔታው በቀጣዮቹ ቀናትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
አልፎ አልፎ የሚታየው ከፍተኛ የዝናብ መጠን በማሳዎች ላይ ውኃ እንዳያቆርር፣ እንዲሁም በከተሞች አካባቢ የውኃ መፋሰሻ ቱቦዎች በመዘጋታቸው ምክንያት ድንገተኛ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ጠይቀዋል። በአዲስ አበባና በሌሎችም አካባቢዎች የሚታየው ከፍተኛ ሙቀትና ወበቅ ከደመና ክምችትና ከፀሐይ ጨረር ነጸብራቅ ጋር የተያያዘ መደበኛ የበልግ ጠባይ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በአንዳንድ አካባቢዎች በሚያጋጥመው ከባድ የዝናብ መጠን ምክንያት የመሬት መንሸራተት፣ የአፈር መሸርሸርና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል በተጋላጭ አካባቢዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: