ከአማራጭ እንክብካቤ ማዕከላት ለሚወጡ ወጣቶች የፖሊሲ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከአማራጭ እንክብካቤ አድገው የወጡ ማህበራት ጥምረት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆነው ዮናስ፤ ወጣቶች አማራጭ እንክብካቤም ማዕከላት (የህጻናት መንደሮች) ከወጡ በኋላ በቂ የመንግስት ድጋፍ እና የፖሊሲ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጡ መሆኑን አስታወቀ። ዮናስ ይህንን የገለጸው ለ #ጌጡ_ተመስገን_ሚዲያና_ኮሙኒኬሽንስ በሰጠው ቃለ ምልልስ ላይ ሲሆን፣ እሱም የሰላም ህጻናት መንደር ፍሬ መሆኑን ጠቅሷል።

ወጣቶቹ ከማዕከላቱ ከወጡ በኋላ የሚገጥሟቸው በርካታ ተግዳሮቶች ያሉ ሲሆን ወጣቶቹ ከእንክብካቤ ማዕከላት ራሳቸውን ችለው ከወጡ በኋላ የመታወቂያ አሰጣጥን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን ለማግኘት ይቸገራሉ ተብሏል።

ወደ ማህበረሰቡ በሚቀላቀሉበት ጊዜ የመንግስት ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች እነዚህን ወጣቶች ያላካተቱ በመሆናቸው ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ይጋለጣሉ።በተጨማሪም ወጣቶቹ ራሳቸውን ችለው ኑሮ ከጀመሩ በኋላ ወድያው ከማህበረሰቡ ጋር ለመቀላቀል እንደሚቸገሩ ተገልጿል።

ወጣቶቹ ማዕከላቱን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በማዕከላቱ ውስጥ ሰባት የተለያዩ የአማራጭ እንክብካቤ ዝግጅቶች እና ምርጫዎች ይቀርቡላቸዋል።

ከእነዚህ የሽግግር አማራጮች ውስጥ የመጨረሻው ወጣቶቹ ማዕከላቱን ለቀው ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን፤ አንዴ ትምህርታቸውን ጨርሰው ወይም ዩኒቨርሲቲ ገብተው ከወጡ በኋላ ወደ ማዕከሉ መመለስ አይፈቀድላቸውም።

ይህን የድጋፍ ክፍተት ለመሙላት ከዚህ ቀደም እንደ ሰላም የህጻናት መንደር እና ኤስ.ኦ.ኤስ ካሉ ተቋማት የወጡ ወጣቶች የየራሳቸው ማህበር በማደራጀት ክፍተቱን ለሞሙላት ሙከራ ተደርጓል።

አሁን ላይ ግን የሁሉንም ድምጽ በአንድ ለማሰማት ሀገር አቀፍ የሆነ ከአማራጭ እንክብካቤ አድገው የወጡ ማህበራት ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን፤ ማህበሩም የራሳቸው ማህበር የሌላቸውን ሌሎች ወጣቶች በማካተት እና በማደራጀት መብታቸውን ለማስከበር እየሰራ ነው ተብሏል።

📷 ከበደ መክብብ

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: