ፋይዳ ማስተሳሰር‼️
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ ጋር ማስተሳሰርን በተመለከተ ውሳኔ አስተላለፈ‼️
የባንኩ መግለጫ ከዚህ በታች ቀርቧል፡-
የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ (ብሔራዊ መታወቂያ) ጋር የማስተሳሰር ስራን በተመለከተ የተላለፈ ውሳኔን ስለማሳወቅ
በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የሚታየውን የማንነት ማረጋገጫ ክፍተት ለመሙላት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ “ፋይዳ” ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን እንደ ቀዳሚ የማንነት መለያ መታወቂያ የመጠቀም ተግባር መጀመሩ ይታወቃል። በተለይም ነባር የባንክ ሂሳቦችን ከፋይዳ ቁጥር ጋር የማስተሳሰር ስራ ከታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ዲሴምበር 24) ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ባንኮች ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።
ይህ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የማስተሳሰር ስራ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ርብርብ ቢከናወንም፣ ከአጠቃላዩ የባንክ ሂሳብ ባለቤቶች ቁጥር አንጻር ሲታይ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተሉትን ነጥቦች ታሳቢ በማድረግ አዳዲስ ውሳኔዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተላልፈዋል፦
በዚህም መሠረት፦
የመመዝገብ አቅም፦ በአሁኑ ወቅት የፋይዳ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ40 ሚሊዮን በላይ መድረሱ፣ በመላው ሀገሪቱ 7 ሺህ የመመዝገቢያ ማሽኖች ተሰማርተው በቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ መሆናቸው እና በሳምንት እስከ 3 ሚሊዮን ሰዎችን የመመዝገብ አቅም መኖሩን፤
የቴክኖሎጂ ዝግጁነት፦ በቀን 2 ሚሊዮን እና ከዚያ በላይ የደንበኛህን እወቅ (e-KYC) አገልግሎት መስጠት የሚችል እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ደንበኞችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ጠንካራ የመሰረተ ልማት ዝግጅት መኖሩን፤ እና
የባንኮች ዝግጁነት፦ ባንኮች በቅርንጫፎቻቸው በአካል በመገኘትም ሆነ በዲጂታል አማራጮች (Links) ደንበኞቻቸውን ለማስተሳሰር ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ የሚከተሉት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
1. ከዚህ በታች በተጠቀሱት 26 ዋና ዋና ከተሞች እና በሐረሪ ክልል የሚገኙ የሁሉም ባንክ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም (May 14, 2026) ድረስ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ቁጥር (ብሔራዊ መታወቂያ) ጋር ማስተሳሰር እና ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።
1. ሀረሪ (Harari) ክልል
2. አዲስ አበባ (Addis Ababa)
3. ድሬዳዋ አስተዳደር (Dire Dawa)
4. ባህር ዳር (Bahir Dar)
5. ጎንደር (Gondar)
6. ደሴ (Dessie)
7. ደብረ ብርሃን (Debre Berhan)
8. ኮምቦልቻ (Kombolcha)
9. ሀዋሳ (Hawassa)
10. አርባ ምንጭ (Arba Minch)
11. ወላይታ ሶዶ (Wolaita Sodo)
12. ሆሳዕና (Hossana)
13. ወራቤ (Worabe)
14. ቡታጅራ (Butajira)
15. ወልቂጤ (Wolkite)
16. ሸገር (Sheger)
17. ጅማ (Jimma)
18. አዳማ (Adama)
19. ሻሸመኔ (Shashemene)
20. ቢሾፍቱ (Bishoftu)
21. ባቱ (Batu)
22. አምቦ (Ambo)
23.መቐለ (Mekelle)
24. አክሱም (Aksum
25. ዓዲግራት (Adigrat)
26. ጋምቤላ ከተማ (Gambela City)
27. አሶሳ (Asosa)
2. በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (July 07, 2026) ድረስ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከላይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሂሳባቸውን የማያስተሳስሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው ከወጪ ወይም ተቀናሽ ግብይት የታገደ (No Debit) የሚሆን ሲሆን፣ እገዳው የሚነሳው ደንበኛው የፋይዳ መታወቂያ ቁጥሩን ከባንክ ሂሳብ ቁጥሩ ጋር ሲያስተሳስር ብቻ ይሆናል።
ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ በላይ የተሰጠው አቅጣጫ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብን እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ነዋሪዎችን አይመለከትም። በውጭ ሀገር የሚገኙ የሂሳብ ባለቤቶች አስፈላጊውን ማስረጃ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት ለባንኮች በማቅረብና በማረጋገጥ ከዚህ ውሳኔ ነፃ መሆን ይችላሉ። በዚህ አጋጣሚ ባንኮች ከዚህ ቀደም በተዘጋጀው ቅጽ መሰረት ሳምንታዊ የአፈጻጸም ሪፖርት መላካቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.