የታይዋን ፕሬዝዳንት የአየር ክልል ተዘግቶባቸው የአፍሪካ ጉዛቸውን ተሰረዘ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የታይዋኑ ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር ኢስዋቲኒ ለማቅናት አቅደው የነበረ ቢሆንም፣ የአየር ክልል ፍቃድ በማጣታቸው ጉዟቸውን ለመሰረዝ ተገደዋል።

ሲሸልስ፣ ሞሪሸስ እና ማዳጋስካር ለፕሬዝዳንቱ በረራ የአየር ክልላቸውን ክፍት ለማድረግ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የታይዋን ፕሬዝዳንታዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ፓን ሜንጋን እንደገለጹት፣ ሀገራቱ ቀደም ሲል ፍቃደኝነታቸውን አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን በድንገት ሃሳባቸውን ቀይረዋል።

ታይዋን ለዚህ የአቋም ለውጥ ዋነኛው ምክንያት ከቤጂንግ (ቻይና) የሚመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጫና መሆኑን በግልጽ ተናግራለች።

​”ቻይና ታይዋንን በዓለም አቀፍ መድረክ በዲፕሎማሲ ለማግለል የምታደርገው ጥረት አካል ነው” — የታይዋን ባለስልጣናት

ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግ ቴ ወደ ስፍራው ማቅናት የፈለጉት፣ የታይዋን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት የኢስዋቲኒው ንጉሥ ሚስዋቲ 40ኛ ዓመት የንግሥና በዓል ላይ ለመታደም ነበር።

ኢስዋቲኒ በአሁኑ ወቅት ለታይዋን ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ እውቅና ከሰጡ 12 የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

​ይህ ክስተት ቻይና የታይዋንን የውጭ ግንኙነት መስመር ለመዝጋት የምታደርገውን ጥብቅ ቁጥጥርና በአፍሪካ ሀገራት ላይ ያላትን የፖለቲካ ተጽዕኖ በድጋሚ ያሳየ ሆኗል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#premiumtimes #Taiwan #Eswatini #China #Africa #Diplomacy #thiqahEth


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1