በታላቅ ድምቀት በአምቦ ከተማ የሚካሄድ ቃላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተዘጋጀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | በአምቦ መሠረተ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ዋና አዘጋጅነት “ማረፊያዬ ይህቺ ናት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሚያዚያ 16 እስከ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአምቦ ከተማ እንደሚካሄድ ታወቀ።

​ይህ መንፈሳዊ መርሐ ግብር በሁለት ዋና ዋና ስፍራዎች የሚከናወን ሲሆን፣ በጉባኤው ላይ በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የሰባቱም አድባራት ካህናት የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን የከተማዋ ምዕመናንና የዩኒቨርሲቲው የግቢ ተማሪዎች በሙሉ በአንድነት የሚያሳትፍ እንደሚሆን ተገልጿል።

​የጉባኤው ዝርዝር መርሐ ግብር

​ጉባኤው ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የሚካሄድባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው።

• ​በአምቦ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ፦ መደበኛው መንፈሳዊ ጉባኤ የሚደረግ ሲሆን፣ ትምህርተ ወንጌልና ልዩ የዝማሬ የምሥጋና መርሐ ግብር የሚከናወንበት ሁኔታ እንዳለ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

• ​እሁድ በ18/2018 ዓ ም ጠዋት ከ1:00 እስከ 2:30 ድረስ የሩጫ ውድድር መነሻውንና መድረሻውን አምቦ መሠ/ሕ ኪዳነምሕረት ቤ/ያን አድርጎ ይከናወናል። ከቀኑ 5:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ ከአምቦ ኪዳነምሕረት እስከ አዋሮ አጫሉ ካምፓስ ስታዲዬም ድረስ የእግር ጉዞ እና የጎዳና ላይ ዝማሬ ይደረጋል

• ከቀኑ 8:00 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:00 ድረስ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አጫሉ ካምፓስ ስቴዲዬም፦ ሰፊውን የአምቦ ሕዝብ እና ያቀፈ የዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰቡንና ወጣቶችን በማሳተፍ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ የወንጌል እና የዝማሬ መድረክ የሚኖር ይሆናል።

​ዓላማው
​“ማረፊያዬ ይህቺ ናት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ጉባኤ፣ በዋናነት ምዕመናን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲበረቱ፣ ሰላምና ፍቅር በከተማዋ እንዲሰፍን እንዲሁም በወጣቱ ዘንድ የሥነ-ምግባርና የታሪክ ግንዛቤ እንዲጎለብት ታስቦ የተዘጋጀ ጉባኤ እንደሆነ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

​በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ መምህራን፣ ዘማርያንና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች አባገዳዎች እና አደ ስንቄዎች እንደሚገኙ ታውቋል። የአምቦ ከተማና አካባቢዋ ማኅበረ ካህናት ኤና መላዋ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያንና የዩኒቨርስቲው የግቢ ጉባኤ ተማራውች በዚህ በረከት ላይ በሦስቱም ቀናት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

​ቀን፡ ከሚያዚያ 16 – 18 ቀን 2018 ዓ.ም
ቦታ፡ አምቦ (ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን እና አጫሉ ካምፓስ ስቴዲዬም)

🔴 የጉባኤው አዘጋጆች፦
የአምቦ መሠረተ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምህረት የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ እና በአዲስ አበባ የሚገኘው ንዑስ የሕንጻ አሠሪ ኮሚቴ በጋራ።




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: