የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
#Ethiopia | ሀገራዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠረታዊ የሆነ የባህል ለውጥ ያስፈልጋል። ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናን እና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን እንገኛለን።
መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የጀመርነው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም፣ በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧል። ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል። ዛሬ በይፋ የተመረቀው የመሶብ የሞባይል አገልግሎትም የዚሁ ቀጣይነት ያለው የሥራ እንቅስቃሴ አካል ነው።
ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል፣ እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን የምንቀጥል ይሆናል።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.