አዲስ-አፍሪካ ሪል ስቴት ኤክስፖ 2026 ሊከፈት ነው!!
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደውና መዲናችን አዲስ አበባን የአፍሪካ የሪል ስቴት እና የኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ ያለመ ታላቅ ኤክስፖ ከሀሙስ ሚያዚያ 15 2018 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም (April 23 – 26, 2026) የሚቆየው ይህ አክስፖ በሳይንስ ሙዚየም (አዲስ አበባ) ይካሄዳል፡፡
📍ኤክስፖው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዚቢሽን እና የአፍሪካ ሪል ስቴት ማህበር (AFRES) የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ጉባኤ ነው፡፡
📍በኤግዚቢሽኑ ላይ የሚሳተፉት የማህበሩ አባላት የሆኑ ታማኝ የሪል ስቴት አልሚዎች ብቻ ናቸው።
📍ዝግጅቱን ልዩ የሚያደርገው ቤት ፈላጊው ማህበረሰብ አስተማማኝ ምርጫ እንዲያገኝ ማድረጉ ነው።
📍ዘመናዊ የቤት ፕሮጀክቶች፣ የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች)፣ የኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች እና አገልግሎት ሰጪዎች በአንድ ጣራ ስር ይገኛሉ ይህም የተሟላ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ ነው ።
📍የአፍሪካ ሪል ስቴት ማህበር (AFRES) ጉባኤ ከአህጉሪቱ የተውጣጡ ባለሀብቶችና አልሚዎች የሚሳተፉበት በመሆኑ ለልምድ ልውውጥና ለጋራ ኢንቨስትመንት ትልቅ እድል ይፈጥራል።
📍ለቤት ፈላጊዎችም በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ አማራጮችን በአንድ ቦታ አነጻጽሮ ለመወሰንና የባንክ ብድር መረጃዎችን ለማግኘት አመቺ መድረክ ነው።
📍ዝግጅቱ ከመደበኛ ባዛር ባለፈ፣ በከተማና መሠረተ ልማትና በአዲስ አበባ ኩተማ አስተዳደር ድጋፍ የሚዘጋጅና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የዘርፉ ተዋንያን የሚሳተፉበት አህጉራዊ ኩነት መሆኑን ማሳየት።
📌 የዝግጅቱ ዋናው ትኩረት “ጥራት፣ እምነት እና አህጉራዊ ትስስር” ላይ ሲሆን ሁላችሁም እንድትጎበኙ ተጋብዛችኋል።
መረጃ ቢያስፈልግዎ፡-0946624646
0910616226 ይደውሉ
አዘጋጆች፦ የኢትዮጵያ የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ከዶክሳ ኢቨንትስ ጋር በመተባበር (በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ)
Source: FastMereja








No comments yet.