በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም አቀፍ የኮንዶም ገበያ ላይ የ30 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትል እንደሚችል የዘርፉ ግዙፍ አምራች ኩባንያ አስታወቀ።
የማሌዢያው ካሬክስ ቢኤችዲ (Karex Bhd) ባወጣው መግለጫ፤ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ግጭት የሚቀጥል ከሆነ የምርቱ ዋጋ ከፍ ሊል እንደሚችል አመልክቷል።
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጎህ ሚያህ ኪያት እንደገለጹት፤ ለዋጋው መጨመር በዋናነት የጭነት ወጪ መናር እና የመርከቦች ጉዞ መዘግየት በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ የፈጠሩት እንቅፋት ምክንያት ሆኗል።
በየዓመቱ 5 ቢሊዮን ኮንዶም የሚያመርተው ኩባንያው፤ አሁን ላይ ያለው የዓለም አቀፍ የጸጥታ ሁኔታ ምርቱን ለገበያ እንዳያቀርብ እንቅፋት እንደሆነበት ገልጿል።
የኮንዶም ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ቢመጣም፤ የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ውጥረት የሎጂስቲክስ ሥራውን እያስተጓጎለው እንደሚገኝ ተመልክቷል።
ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፤ ይህ የዋጋ ጭማሪ ሥጋት በተለይ በአቅርቦት እጥረት ላይ ባሉ ሀገራት ላይ የጤና ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይጠበቃል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.