የውጭ አገር ስራ ስምሪት ሂደቱን የሚያከናውኑ ኤጀንሲዎች ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ በተደረገ ጥብቅ ክትትል፣ ህግ ጥሰው በተገኙ ከ200 በላይ ኤጀንሲዎች ላይ የእግድ እርምጃ መወሰዱን ስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።
እርምጃው የተወሰደው በሰራተኞች ላይ በደል ካደረሱ፣ የደመወዝ ክፍያ ካዘገዩ እና ሰነዶችን ካጭበረበሩ ኤጀንሲዎች ላይ ነው።
አዲሱ የቴክኖሎጂ ስርዓት ማንኛውም ኤጀንሲ ያለበትን ቅሬታ ወይም ያለመግባባት በወቅቱ ካልፈታ፣ ሲስተሙ በራሱ ኤጀንሲውን “ብሎክ” የሚያደርግበት አሰራር ተዘርግቷል።
ይህም ማለት ኤጀንሲው ተጨማሪ ሰራተኞችን መላክም ሆነ የስራ ውል ማሳደስ አይችልም።
በተለይም በውጭ አገር ችግር የደረሰባቸው ዜጎች ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ፣ ኤጀንሲው ችግሩን ፈትቶ የዜጋውን ደህንነት ማረጋገጡ በሲስተሙ እስካልታየ ድረስ ስራውን መቀጠል አይችልም።
ይህም ኤጀንሲዎች ለዜጎች መብትና ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ የሚያስገድድ እንደሆነ ተገልጿል።
ሊዲያ ደሳለኝ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.