በበርካታ የዓለም ሀገራት ከፍተኛ ዝናን እና ተቀባይነትን ያተረፈው ኤኮ ጫማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በይፋ ገባ!
ከ1963 እ.አ.አ ጀምሮ የዴንማርኩ ግዙፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ጥራቱ፤ በምቾቱ እንዲሁም በፈጠራው ቀዳሚ የሆነው ታዋቂው የጫማ ብራንድ ‘ኤኮ’ (ECCO) በበርካታ የዓለም ሀገራት ከፍተኛ ዝናን እና ተቀባይነትን ያተረፈ ተቋም ነው፡፡
ምንም እንኳን ይህ ዓለም አቀፍ ብራንድ ትልቅ ስም ቢኖረውም እስካሁን በሀገራችን ገበያ ላይ በስፋት አልነበረም። አሁን ግን ኦተንቲከ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (Authentic Business PLC) የዚህ ግዙፍ ኩባንያ ይፋዊ አጋር (Official Partner) በመሆን፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የኤኮ (ECCO) ምርቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በይፋ አስገብቷል።
የዚህን ግዙፍ ብራንድ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት እና ይፋዊ ስራ መጀመር አስመልከቶ፣ዛሬ ሐሙስ፣ ጃፓን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው ናይል ሶርስ ህንፃ (Nile Source Building) ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
ካርል ሄንዝ ዌርነር በተለይ በዴንማርክ ኤኮ የተሰኘ ጫማዎችን በማምረት የሚታወቅ ኩባንያን የመሰረተ ሰው ነው።
ኤኮ ጫማ ለአገራችን አየር ንብረት ተስማሚ ሆኖ የተሰራ መሆኑንም አቶ ስለሺ ብርሀኑ የAuthentic Business PLC ማኔጀር ገልፀዋል።



Source: Yeneta Tube









No comments yet.