በ1.9 ቢሊዮን ብር የተገነባው ኃይሌ ሆቴል ደብረ ብርሃን ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja | በታዋቂው አትሌትና ኢንተርፕረነር ኃይሌ ገብረስላሴ ባለቤትነት የሚመራው የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ፣ በ1.9 ቢሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን ዘመናዊ ሆቴል ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ በድምቀት አስመረቀ። ሆቴሉ የድርጅቱ 11ኛ መዳረሻ ሆኖ ተመዝግቧል።

​ይህ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት በኢንዱስትሪ ከተማዋ ደብረ ብርሃን ያለውን ከፍተኛ የእንግዳ ማረፊያ ፍላጎት ለመሙላትና የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ ተገልጿል። ሆቴሉ በህንፃ ጥራቱና በውስጡ በያዛቸው ዘመናዊ መገልገያዎች በከተማዋ ቀዳሚ ተጠቃሽ ሆኗል።

​በ1.9 ቢሊዮን ብር የተገነባው ይህ ሆቴል፣ ለታላላቅ እንግዶችና ለቱሪስቶች ምቹ የሆኑ 123 መኝታ ክፍሎችን ይዟል። ከዚህም በተጨማሪ አራት የተለያዩ ሬስቶራንቶች፣ የመጠጥ አገልግሎት የሚሰጡ ባሮች፣ ጂምና የሳውና አገልግሎቶችን ያካተተ ነው። ትላልቅ ስብሰባዎችንና ማህበራዊ ኩነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችሉ ስድስት ዘመናዊ አዳራሾችም ተገንብተውለታል።

​የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩፕ ባወጣው መረጃ መሰረት፣ ሆቴሉ በአሁኑ ወቅት ለ200 በላይ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ በቀጣይ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የሠራተኞቹ ቁጥር ወደ 300 ከፍ እንደሚል ታውቋል።

ሻለቃ ኃይሌ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገረው​በቀጣይ በጎንደር፣ በሐረር እና በድሬዳዋ ከተሞች የሚገነቡ ሆቴሎችን በማጠናቀቅ ለምረቃ እንደሚያበቃ ተጠቁሟል። ይህም ድርጅቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የኢንቨስትመንት አሻራ ይበልጥ እንደሚያሰፋው ታምኖበታል። ከኢትዮጵያ ውጪ ኃይሌ ሆቴል በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ለማስፋት እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ተነግሯል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: