ትራምፕ በኢራን ሊገደሉ የነበሩ 8 ሴቶችን ከሞት ታደጉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ዓለምን ያስደመመ ዲፕሎማሲ! ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ ስምንት ሴት ተቃዋሚዎች በእርሳቸው ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና ጥያቄ ከሞት ቅጣት መትረፋቸውን በይፋ አስታወቁ።

​ ከስምንቱ ሴቶች መካከል አራቱ ወዲያውኑ እንዲፈቱ፣ ቀሪዎቹ አራቱ ደግሞ የአንድ ወር እስራት ብቻ ተፈርዶባቸው እንዲቆዩ ከኢራን መሪዎች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል።

​ትራምፕ በ”ትሩዝ ሶሻል” ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የኢራን መሪዎች የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በመሆናቸው ያቀረቡትን ጥያቄ በማክበራቸው “ከፍተኛ ምስጋና” እንዳላቸው ገልጸዋል።

ይህ እርምጃ በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ለሰላም ድርድር አዲስ በር ሊከፍት እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት “እኔ ከመጣሁ ጦርነት ይቆማል” ያሉትን ቃል በተግባር እያሳዩ ይመስላል። የኢራን መሪዎች ለትራምፕ ጥያቄ እንዲህ ያለ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸው፣ ከትራምፕ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ለመደራደር ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል። ይህ “የድርድር ጥበብ” (Art of the Deal) ውጤት ይሆን?

​ዲፕሎማሲው ከጦርነቱ ድምጽ ይልቅ እያየለ ነው!

​#getu #BreakingNews #TrumpIran #HostageRelease #Diplomacy #HumanRights #ArtOfTheDeal #MiddleEastPeace #TrumpNews #ትራምፕ #ኢራን #ዲፕሎማሲ #ሰበርዜና #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: