መንግሥት ካሮት እና ስኳር ድንች ከአየር ላይ ወደ ምድር በተነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ለአደጋ የተጋለጡ የዱር እንስሳትን ከረሃብ ለመታደግ በሺዎች የሚቆጠር ኪሎግራም ካሮት እና ስኳር ድንች ከአውሮፕላን ላይ ተበተነ።

በአውስትራሊያ በደረሰው ከባድ ድርቅ ምክንያት የተፈጥሮ ምግብ አቅርቦታቸው የተቋረጠባቸውንና ለጥፋት የተቃረቡትን “ብሩሽ-ቴይልድ ሮክ ዋላቢ” (Brush-tailed rock wallabies) የተሰኙ ብርቅዬ እንስሳትን ለማዳን መንግሥት አስገራሚ እርምጃ ወስዷል።

ባለሥልጣናቱ እንስሳቱ በሚገኙባቸው ርቀው በሚገኙና ለሰው ልጅ ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ተራራማ አካባቢዎች ላይ በሺዎች የሚቆጠር ፓውንድ ካሮትና ስኳር ድንች ከአየር ላይ እንዲዘንብ አድርገዋል።

ይህ ያልተለመደ የነፍስ አድን ተልዕኮ እንስሳቱ በድርቅ ምክንያት ከሚገጥማቸው የረሃብ ሞት እንዲተርፉ ትልቅ ተስፋ ሆኗቸዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ይህ ዓይነቱ ድጋፍ እንስሳቱ የተፈጥሮ መኖሪያቸው እስኪያገግም ድረስ ሕይወታቸውን ለማቆየት ወሳኝ ነው።

እንደ መናኽሪያ ኤፍ ኤም ዘገባ ለእንስሳት መብትና ደህንነት ትልቅ ትኩረት የሰጠው ይህ ተግባር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ያስደነቀና የአውስትራሊያን ቁርጠኝነት ያሳየ ሆኖ ተመዝግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1