የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ከአርሰናል ነጠቀ
#Ethiopia | የኤርሊንግ ሃላንድ ቀድሞ የተቆጠረች ጎል ማንችስተር ሲቲን ወደ ሰንጠረዡ አናት መርታዋለች። ሲቲ ባርንለይን 1 ለ 0 በማሸነፍ፣ አርሰናል ለረጅም ወራት ተቆጣጥሮት የነበረውን መሪነት በይፋ ተረክቧል።
ባርንለይ 0-1 ማንችስተር ሲቲ
ኤርሊንግ ሃላንድ (5′)
ማንችስተር ሲቲ ይህንን ድል ተከትሎ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ በአንጻሩ መድፈኞቹ (አርሰናል) ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ለማለት ተገደዋል። የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ሽኩቻ አሁን አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
ሲቲዎች በልምድ የታጀበው ግስጋሴያቸው አሁንም ዋጋ እያስገኘላቸው ይገኛል። አርሰናል ለረጅም ጊዜ መሪነቱን ቢይዝም፣ አሁን ግን ዋንጫው እጁ ላይ እንዲቆይ ጠንካራ ትግል ማድረግ ይኖርበታል። ሃላንድ አሁንም ለቡድኑ ወሳኝ ጎሎችን ማስቆጠር መቻሉ ለፔፕ ጋርዲዮላ ትልቅ እፎይታ ነው።
የሊጉ ፉክክር አሁን ተጋጋለ
#getu #ManchesterCity #Arsenal #PremierLeague #Haaland #FootballNews #TitleRace #EPL #ማንችስተርሲቲ #አርሰናል #ፕሪሚየርሊግ #ሃላንድ #ስፖርት #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.