ኢራን ለተኩስ አቁም ስምምነቱ እውቅና እንደማትሰጥ አስታወቀች
በመካከለኛው ምስራቅ የነበረው ደካማ ሰላም አደጋ ላይ ወድቋል፤ ቴህራን ወታደራዊ እርምጃ ልወስድ እችላለሁ በማለት ዝግጅቷን እያሳየች ነው።
የኢራን መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን ባስተላለፉት አስቸኳይ መረጃ መሠረት፣ ሀገሪቱ በቅርቡ የተደረሰውንና የተራዘመውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደማታውቀው በይፋ ገልጻለች። የቴህራን ባለሥልጣናት እንደተናገሩት ከሆነ ኢራን በማንኛውም ስምምነት የምትገዛው የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ብቻ መሠረት በማድረግ ሲሆን፣ ይህንን ጥቅሟን ለማስከበር ስትልም አስፈላጊውን ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ወደኋላ እንደማትል ፍንጭ ሰጥተዋል።
ይህ ያልተጠበቀ አቋም ቀጣናውን ወደ ከፍተኛ ውጥረትና አለመረጋጋት የከተተው ሲሆን፣ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት አሁን ላይ የመፍረስ አደጋ ተጋርጦበታል። የኢራን ባለሥልጣናት በሰጡት ማብራሪያ ሀገራቸው ለማንኛውም ዓይነት የኃይል እርምጃ ዝግጁ መሆኗን በማሳሰብ፣ ቀጣይ ውሳኔዎቻቸው በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታዎችና በብሔራዊ ደህንነታቸው ላይ ብቻ የተመሰረቱ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.