ዓለም አቀፉ ኤኮ (ECCO) ጫማ በኢትዮጵያ ተከፈተ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja: በዓለም አቀፍ ደረጃ በቆዳ ውጤቶችና በጫማ ምርቶቹ ዝነኛ የሆነው የዴንማርኩ ኤኮ (ECCO) ኩባንያ በኢትዮጵያ ገበያ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ኩባንያው በተለይ የራሱን ቆዳ በማምረትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከምቾት ጋር በማዋሃድ የሚታወቅ ሲሆን፣ “ጫማ እግርን መከተል አለበት እንጂ እግር ጫማን መከተል የለበትም” የሚለውን መርህ እንደሚከተል የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

የኤኮ ጫማዎች በዓለም ገበያ ተመራጭ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች መካከል ድርጅቱ የራሱ የቆዳ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ያሉት መሆኑ ዋነኛው ሲሆን፣ ይህም የቆዳውን ጥራት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቆጣጠር ያስችለዋል።

በተጨማሪም FLUIDFORM™ የተሰኘውን የላቀ የፈሳሽ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የጫማውን ሶል (Sole) እና የላይኛውን ክፍል ያለ ስፌት ወይም ሙጫ በማገናኘት፣ ጫማው ዘላቂ፣ ቀላልና ተለዋዋጭ እንዲሆን እንደሚያደርገው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የኤኮ ጫማዎች ብቸኛ ተወካይ ሆኖ የተሰየመው አውተንቲክ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር(Authentic Business PLC) ১০: ১০५८ የኤኮ ጫማዎችን በታማኝነትና በከፍተኛ ጥራት ከዚህ ድርጅት ማግኘት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

የአውተንቲክ ቢዝነስ ኃላፊዎች እንዳመለከቱት፣ ኩባንያው የኤኮን ምርቶች ወደ አገር ውስጥ ማስገባት መጀመሩ ለተጠቃሚዎች የጥራት አማራጭ ከመፍጠሩ ባለፈ፣ በቀጣይነት ተጨማሪ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

ይህ የዓለም አቀፍ ብራንድ ወደ ኢትዮጵያ መግባት በአገሪቱ የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረዉ ተገልጿል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1963 በካርል ሄንዝ ዌርነር የተመሠረተው ኤኮ፣ በዓለም ዙሪያ በብዙ አገራት ሰፊ ተቀባይነትና እውቅና ያለው ግዙፍ ተቋም ነው፡፡

📷 ከበደ መክብብ






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1