የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጦር መሣሪያዎችን በዘመናዊ ዳታቤዝ መመዝገብ ጀመረ
ፌደራል ፖሊስ በተቋሙ ግምጃ ቤትና በአባላቱ እጅ የሚገኙ የጦር መሣሪያዎች ላይ ምልክት የማድረግና ወደ ዘመናዊ የመረጃ ቋት የማስገባት ሥራ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
አዲሱ አሠራር በሀገር አቀፍ ደረጃ የትኛው የጦር መሣሪያ የት እንደሚገኝ በቀላሉ ለማወቅና ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሏል።
ምልክት የማድረጉ ሥራ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት፣ የጠፉ መሣሪያዎችን ለመለየትና በጦር መሣሪያ የታገዙ ወንጀሎችን ለመመርመር ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ተጠቁሟል።
የምዝገባ ሶፍትዌሩና የመረጃ ቋቱ በፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የበለፀገ መሆኑ ተመላክቷል።
👉 በፌደራል ደረጃ የተጀመረው ይህ ምዝገባ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደር ፖሊስ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።ስፑትኒክ
@seledadotio

No comments yet.