#Ethiopia | በስደስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በግላቸው ተወዳድረው ፓርላማ የገቡት ዳንኤል ክብረት፣ ዘንድሮ በሚካሄደው ሰባተኛው ምርጫ ግን ብልጽግናን ተቀላቅለዋል፤ እጩ ሆነውም ቀርበዋል።
በእርግጥ በ2013ቱ ምርጫም ብልጽግና በአዲስ አበባ ዕጩ ያላቀረበበት የምርጫ ክልል ዳንኤል የተወዳደሩበት ብቻ ነበር።
ምንም እንኳን የእንደራሴዎች መቀመጫን አሸንፈው በግላቸው ፓርላማውን ቢቀላቀሉም ቢያንስ አዲስ ማለዳ ተገኝታ በተከታተለቻቸው እና በቀጥታ ሥርጭት በተላለፉ መደበኛም ይሁን አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይ ዳንኤል ጥያቄ ሲያቀርቡ አልያም አስተያየት ሲሰጡ አልተስተዋለም።
ዳንኤል የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ መሆናቸውም ይታወቃል ስትል የዘገበችው አዲስ ማለዳ ናት።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
##getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.