1.9 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ኃይሌ ሆቴል በደብረብርሃን ከተማ ተመርቆ ስራ ጀመረ
የሀይሌ ሆቴሎች ከ16 ዓመታት በፊት ጅማሮውን ያረገ ሲሆን 11ኛ ሪዞርቱን በደብረብርሃን በዛሬው እለት አስመርቋል።
ከአዲስ አበባ በ130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የአማራ ብሔራዊ ክልል ውስጥ በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ላይ የተገነባው ይህ ሆቴል የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አቶ መካሻ አለማየሁ እና የከተማዋ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ተገኝተዋል።
ደብረ ብርሃን ከተማ በታሪክ የምትታወቅ እና አዲስ የኢኮኖሚ ማዕከል እየሆነች የመጣች ከተማ መሆናን የተናገረው አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ከተማዋ ኢንዱስትሪን ተገን በማድረግ ኢንቨስትመንትን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሻገረች ትገኛለች ሲል ገልጿል።
ኃይሌ ሆቴል ደብረብርሃን 123 አልጋዎች ያሉት ሲሆን ከ200 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ተወላጆች የስራ እድል ፈጥራል።
ኃይሌ ሆቴሎች ባለፉት ሁለት ዓመታት በወላይታ ሶዶ እና ጅማ ከተሞች ያስገነባቸውን አዳዲስ ሆቴሎች አስመርቆ ወደስራ ያስገባ ሲሆን በሻሸመኔም ጉዳት የደረሰበትን ሪዞርት ዳግም ወደስራ አስገብቷል።
ቀጣይም የሀይሌ ሆቴሎች በድሬደዋ ፣ ሀረር እና ወደሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እንደሚሻገርም ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.