4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት የጎዳና ላይ ሩጫ እሁድ ይካሄዳል

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia| ​የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው አራተኛው የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ “ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ቃል በመጪው እሁድ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

​ይህ የሩጫ ውድድር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት የተጀመረው የ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ አካል ሲሆን አላማውም የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ በማነቃቃት የሀገር ውስጥ ፍላጎትን መሸፈንና ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት መፍጠር ነው።

​የውድድሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለጹት ዝግጅቱ የአምራች ኢንዱስትሪውን ከማስተዋወቅ ባለፈ በሀገር ውስጥ የተመረቱ የስፖርት ትጥቆችን ለተሳታፊዎች በማቅረብ ረገድ ትልቅ ፋይዳ አለው።

​በውድድሩ ላይ ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡና በግል የሚሳተፉ ከ500 በላይ ፕሮፌሽናል አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን በአጠቃላይ ከአስራ አምስት ሺህ በላይ ሯጮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ዲፕሎማቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

​በዕለቱም በሁለቱም ጾታዎች አንደኛ ለሚወጡ አትሌቶች 550 ሺህ ብር፣ ሁለተኛ ለሚወጡ 300 ሺህ ብር እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጡ 200 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል።

​የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውድድሩን በ2019 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስመዝገብና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያከናወነ እንደሚገኝም ታውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1