🙏
የሚያገኛቸውን መከራ ሳይፈሩ ስለ ክርስቶስ አምላክነት ከመስከሩ የክብር አክሊል ከተቀዳጁ ሰማዕታት የሦስት ዓመቱ ሕጻን ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ቅድስት ኢየሉጣ የሮም ግዛት በሆነው አንጌቤን በክርስትና ሃይማኖት ጸንታ የምትኖርና ልጇ ቅዱስ ቂርቆስንም በስርዓት ያሳደገችው ደግ ሴት ነበርች፡፡ በዘመኑ የነበረውን አረማዊ አስተዳዳሪ እለእስክንድሮስን በመፍራት ከልጇ ጋር ከሮም ወደ ጠርሴስ ብትሰደድም እለእስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታም አገኛት።
ወታደሮችም እርሷንና ልጇን ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧቸው። መኮንኑም “ስምሽን ንገሪኝ” ቢላት “ስሜ ክርስቲያን ነው” አለችው። መኮንኑ በብስጭት ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንም “ስምህን ንገረኝ” ሲለው “ስሜ ክርስቲያን ነው፤ እናቴ የሰየመችኝን ከፈለክ ግን ቂርቆስ ነው” ሲል መለሰለት። ቅድስት ኢየሉጣንም “ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል” ሲላት “የምንሰግድለት አንድ ክርስቶስ ብቻ ነው” አለችው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስም እየደጋገመም “እኔ ክርስቲያን ነኝ” ብሎ በመጮሁ ምላሱን ቢያስቆረጠው እግዚአብሔር ፈውሶታል፡፡
መኮንኑ መከራ አጸናባቸው፤ በግርፋት የጀመረ ስቃይ ሊሰሙት ወደ ሚጨንቅ መከራ ቀጠለ። በፈላ ውሃ ውስጥ ሲከታቸውም ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው፡፡ እናትና ልጅ በክርስቶስ ታምነዋልና ጸኑ።
ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላም ጥር 15 ቅዱስ ቂርቆስን ጥር 16 ደግሞ ቅድስት ኢየሉጣን ሰይፏቸው ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡ የሕጻኑን ሥጋ በሠረገላ ኤልያስ አኑሮታል፣ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።
ዛሬም በየገዳማቱ ዓለምን ንቀው የሚኖሩ መነኮሳትና ገዳማውያን በጸሎታቸው ኃይል ያደርጋሉ፡፡ ከዓለም ክብር የክርስቶስን ክብር፣ ከሥጋ ደስታ መንግስተ ሰማያትን መርጠዋልና፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Source: FastMereja









No comments yet.