ቼልሲ አሠልጣኝ ሊያም ሮዘኒየርን አሰናበተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የ 41 ዓመቱ አሠልጣኝ ሊያም ሮዘኒየር ባለፈው ጥር ወር እስከ 2032 በሚደቆይ ኮንትራት ክለቡን ቢረከቡም አራት ወር ሳይሞላቸው ከስልጣናቸው መሰናበታቸው ይፋ ሆኗል።

ሊያም ሮዘኒየር ቡድናቸው ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳያስቆጥር ሽንፈት ማስተናገዱ ለስንብታቸው ምክንያት ሲሆን በ 114 ዓመታት የክለቡ ታሪክ ውስጥም መጥፎ ጉዞ ሆኖ ተቀምጧል።

ዛሬ በኮብሃም አስቸኳይ ስብስባ ያደረጉት የቼልሲ አመራሮች አሠልጣኝ ሊያም ሮዘኒየርን ለማሰናበት ሲወስኑ በምትካቸውም ካሉም ማክፋርሌን ክለቡን በጊዜያዊነት እንደሚመሩ ይፋ ተደርጓል።

ማክፋርሌን ከዚህ ቀደም ኢንዞ ማሬስካ ሲሰናበቱ ክለቡን በጊዜያዊነት የመሩ ሲሆን ከማንችስተር ሲቲ ጋር ነጥብ ተጋርተው በፉልሃም ተሸንፈዋል።
ቼልሲ ባወጣው ይፋዊ መግለጪ ውሳኔውን መወሰን ቀላል እንዳልነበረ ገልፆ ነገር ግን የክለቡ ወቅታዊ አቋም ከሚፈለገው ደረጃ በታች ሆኖ መገኘቱን ጠቅሷል።

ሰማያዊዎቹ አክለውም ለአሠልጣኝ ሮዘኒየር በቀጣይ ህይወታቸው ስኬትን ተመኝተዋል።

ከ 1912 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ምንም ግብ ማስቆጠር ሳይችል የተሸነፈው ቼልሲ በሳምንቱ መጨረሻ በኤፍ ኤ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይጫወታል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #nbc


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1