#Ethiopia | በኢራን መንግስት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ ስምንት ሴት ተቃዋሚዎች፣ በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከሞት ቅጣት መትረፋቸው በይፋ ተነገረ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን የምስራች በማህበራዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ሲደረግ የነበረው ረጅም ድርድር ስኬታማ በሆነ መንገድ መጠናቀቁን አረጋግጠዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ፣ ስምምነቱ በሁለት መልክ ተግባራዊ ሆኗል፦
አራቱ ሴቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ተወስኗል።
ቀሪዎቹ አራቱ ደግሞ የነበረባቸው የሞት ፍርድ ተሰርዞ፣ በአንድ ወር ቀላል እስራት ብቻ እንዲቀጣ ተደርጓል።
ይህ ያልተጠበቀ እርምጃ ለዓመታት ሻክሮ በቆየው በአሜሪካ እና በኢራን ግንኙነት መካከል አዲስ የሰላም ተስፋ ጭሯል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለኢራን መሪዎች ምስጋናቸውን በማቅረብ፣ ይህ ውሳኔ ለወደፊት የሁለቱ ሀገራት የሰላም ድርድር እንደ “ትልቅ የመልካም ፈቃድ ማሳያ” እንደሚቆጠር ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ዜናውን በደስታ እየተቀበሉት ሲሆን፣ ድርጊቱ በዲፕሎማሲ አማካኝነት የሰው ልጆችን ሕይወት መታደግ እንደሚቻል ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ትራምፕ #ኢራን #የሰብዓዊመብት #ዲፕሎማሲ #ሰላም #Trump #Iran #HumanRights #PeaceAgreement
Source: GetuTemesgen









No comments yet.