በአንጋፋው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ላይ እየደረሰ ያለው ጫና እና ወከባ ህግን በጣሰ መልኩ ይበልጥ አደገኛ እርምጃ ወዳለበት ደረጃ መሸጋገሩ ተጋለጠ።
የፌዴራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ፣ መሳሪያ የታጠቁ እና በፌዴራል ፖሊስ ተሽከርካሪ የመጡ ታጣቂዎች፣ ሲኤምሲ አካባቢ የሚገኘውን የቴዲ አፍሮ የግል ስቱዲዮ እና ቢሮ በኃይል ሰብረው መግባታቸውን የዓይን እማኞች እና የቅርብ ምንጮች አረጋግጠዋል።
ይህ ህገ-ወጥ የኃይል እርምጃ የተፈጸመው ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ መሆኑ የታወቀ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ወደ ስቱዲዮው ጥሶ ለመግባት የህንጻውን ጥበቃ (ዘበኛ) በከፍተኛ ሁኔታ መደብደባቸው ተገልጿል።
የህግ አስከባሪ አካላት መደበኛውን የህግ አግባብ እና የፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ ወደ ጎን በመተው፣ በምሽት የዜጎችን የስራ ቦታ እና የግል ንብረት በኃይል መስበራቸው የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት እና የዜጎችን ደህንነት ክፉኛ ጥያቄ ውስጥ የሚከት ድርጊት ሆኗል።
ከዚህ የኃይል እርምጃ ባሻገር የጉዳዩን አሳሳቢነት እጅግ ከፍ የሚያደርገው የተሰበረው ቢሮ ይዘት እና የተወሰዱት ንብረቶች ጉዳይ ነው።
ይህ ስቱዲዮ ቴዲ አፍሮ እንደ ዋና ቢሮ የሚጠቀምበት፣ የፈጠራ ስራዎቹን የሚያዘጋጅበት፣ ለህዝብ ጆሮ ያልደረሱ አዳዲስ የሙዚቃ ስራዎቹ እና ግጥሞቹ የሚገኙበት፣ እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦቹን የሚጽፍበት እጅግ ሚስጥራዊ እና ጥብቅ የጥበብ ማህደር ነው።
በስፍራው በርካታ እና ውድ የሆኑ አዕምሯዊ ንብረቶች የሚገኙ ሲሆን፣ አሁን በወጡ አዳዲስ መረጃዎች መሰረት ሰብረው የገቡት የፖሊስ አባላት ከስቱዲዮው ውስጥ ሁለት ላፕቶፖችን፣ ስፒከሮችን፣ የሙዚቃ ማቀናበሪያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የተለያዩ የስቱዲዮ እቃዎችን ወስደዋል።
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.